ኢዮብ 21:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገዱን በፊቱ የሚናገር ማን ነው? እርሱ የሠራውንስ የሚመልስበት ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግባሩን ፊት ለፊት የሚነግረው ማን ነው? የእጁንስ ማን ይሰጠዋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ መንገዱ ፊቱ ለፊት የሚወቅሰው ማን ነው? ስለ ሠራውስ የሚቀጣው ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉውን ሰው ስለ መጥፎ ጠባዩ የሚወቅሰው ማን ነው? በክፉ ሥራውስ የሚቀጣው ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መንገዱን በፊቱ የሚናገር ማን ነው? የሠራውንስ የሚመልስበት ማን ነው? |
በድለናል፤ ዋሽተናልም፤ አምላካችንንም መከተል ትተናል፤ ዐመፃን ተናግረናል፤ ከድተንሃልም፤ የኀጢአትንም ቃል ፀንሰን፤ ከልብ አውጥተናል።
እርሱም ስለ ጽድቅና ስለ ንጽሕና፥ ስለሚመጣውም ኵነኔ በነገራቸው ጊዜ በዚህ የተነሣ ፊልክስ ፈራና ጳውሎስን፥ “አሁንስ ሂድ፤ በተመቸኝም ጊዜ ልኬ አስጠራሃለሁ” አለው።
ወንድሞቻችን፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ ቍጣን አሳልፏት፥ “እኔ እበቀላለሁ፤ እኔ ብድራትን እከፍላለሁ ይላል እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአልና።
የሚጠሉትን ለማጥፋት በፊታቸው ብድራት ይመልስባቸዋል፤ ለሚጠላው አይዘገይም፤ ነገር ግን በፊቱ ብድራትን ይመልስበታል።