ኢዮብ 21:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥንቱን ዕውቀትንና ምክርን የሚያስተምር እግዚአብሔር አይደለምን? በነፍሰ ገዳዩስ የሚፈርድ እርሱ አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርድ አምላክ፣ ዕውቀትን ሊያስተምረው የሚችል አለን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍ ከፍ ባሉት ላይ ለሚፈርደው እግዚአብሔር ሰው እውቀትን ሊያስተም ይችላልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በታላላቅ ሰዎች ላይ እንኳ ይፈርዳል፤ ታዲያ፥ ሰው ለእርሱ የፍርድን ዕውቀት ሊያስተምር ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፍ ከፍ ባሉትስ ላይ ለሚፈርድ ለእግዚአብሔር በውኑ ሰው እውቀትን ያስተምራልን? |
“በውኑ የሚከራከር ሰው ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር ይከራከራልን? ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋቀስ እርሱ ይመልስለት።”
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድርጌ ሠራሁህ፤ ምድርን የሚያርስ ሁልጊዜ ያርሳልን? ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? እጅ የለህምና መሥራት አትችልም ይለዋልን? ጭቃ ሠሪውን ይከራከረዋልን?
መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።