ኢዮብ 21:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወደደውን በቤቱ ውስጥ ያደርጋል። ወራቶቹም ከቍጥር ድንገት ይጐድላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ወራቱ በተገባደደ ጊዜ፣ ለቀሪ ቤተ ሰቡ ምን ይገድደዋል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወራታቸውስ ቍጥር ከተቈረጠ፥ ከእነርሱ በኋላ የቤታቸው ደስታ ምን ይሆናቸዋል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ከሞተ በኋላ፥ ስለ ልጆቹ ምን ደንታ ይኖረዋል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወራታቸውስ ቍጥር ቢቈረጥ፥ ከእነርሱ በኋላ የቤታቸው ደስታ ምን ይሆናቸዋል? |
በምድር ላይ አንድ ቀንም እንኳ ቢኖር፤ ወሮቹም በአንተ ዘንድ የተቈጠሩ ናቸው፤ ዘመኑንም ወስነህ ትሰጠዋለህ፤ እርሱም ከዚያ አያልፍም።
ጥንቱን ዕውቀትንና ምክርን የሚያስተምር እግዚአብሔር አይደለምን? በነፍሰ ገዳዩስ የሚፈርድ እርሱ አይደለምን?