ኢዮብ 21:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣን መብራት ትጠፋለች፤ መቅሠፍትም ትመጣባቸዋለች። የበቀል ቍጣም ይይዛቸዋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የኀጢአተኞች መብራት የጠፋው ስንት ጊዜ ነው? የእግዚአብሔር ቍጣ መከራ የመጣባቸው፣ መቅሠፍትም የደረሰባቸው ስንት ጊዜ ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የክፉዎች መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቁጣው መከራ የከፈላቸው፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለመሆኑ የክፉ ሰዎች መብራት ጠፍቶ ያውቃልን? መቅሠፍትስ በእነርሱ ላይ ወርዶ ያውቃልን? እግዚአብሔር በቊጣው ቀጥቶአቸው ያውቃልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃጥአን መብራት የጠፋው፥ መቅሠፍትም የመጣባቸው፥ እግዚአብሔርም በቍጣው መከራ የከፈላቸው፥ |
እግዚአብሔር የአሕዛብን ምክር ይመልሳል፥ የሕዝቡንም ዐሳብ ይመልሳል። የአለቆችን ምክራቸውን ያስረሳቸዋል።
ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
የዚያ አገልጋይ ጌታ ባልጠረጠረው ዕለት፥ ባላወቀውም ሰዓት መጥቶ ከሁለት ይሰነጥቀዋል፤ ዕድሉንም ከማይታመኑ ጋር ያደርገዋል።