በምክራቸው ሰውነቴ አትገናኛቸው፤ ዐሳቤም በአመፃቸው አትተባበርም፤ በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፤ በገዛ ፈቃዳቸውም የሀገርን ሥር ቈርጠዋልና።
ኢዮብ 21:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እነሆ፥ በጎነታቸው በእጃቸው ውስጥ አለች፤ የኃጥኣንን ሥራ አይመለከትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁንና ብልጽግናቸው በእጃቸው አይደለም፤ ከኀጢአተኞች ምክር እርቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? የክፉዎች ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህንንም የሚሉት በእጃቸው ያለው ሀብት ሁሉ በራሳቸው ጥረት የተገኘ ስለሚመስላቸው ነው፤ እኔ ግን የክፉ ሰዎችን ሐሳብ አልቀበልም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ ሀብታቸው በእጃቸው ውስጥ አይደለምን? የኃጥአን ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት። |
በምክራቸው ሰውነቴ አትገናኛቸው፤ ዐሳቤም በአመፃቸው አትተባበርም፤ በቍጣቸው ሰውን ገድለዋልና፤ በገዛ ፈቃዳቸውም የሀገርን ሥር ቈርጠዋልና።
እንዲህም አለ፥ “ከእናቴ ማኅፀን ራቁቴን ወጥቻለሁ፥ ራቁቴንም ወደ ምድር እመለሳለሁ፤ እግዚአብሔር ሰጠ፥ እግዚአብሔርም ነሣ፤ እግዚአብሔርም እንደ ፈቀደ ሆነ የእግዚአብብሔር ስም የተባረከ ይሁን።”
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
ጌታውም ጠርቶ፦ ‘በአንተ ላይ የምሰማው ይህ ነገር ምንድን ነው? እንግዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ’ አለው።
አብርሃም ግን እንዲህ አለው፦ ‘ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ተድላና ደስታ እንዳደረግህ፥ አልዓዛርም እንዲሁ ሁልጊዜ በችጋር እንደ ነበረ ዐስብ፤ አሁን ግን እንዲሁ እርሱ በዚህ ፈጽሞ ተድላና ደስታ ያደርጋል፤ አንተ ግን መከራ ትቀበላለህ።