ኢዮብ 21:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፤ በሲኦል ማረፊያም ይጋደማሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዕድሜያቸውን በተድላ ያሳልፋሉ፤ በሰላምም ወደ መቃብር ይወርዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፥ በሰላምም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕድሜአቸውን በተድላ ደስታ ያሳልፋሉ፤ ያለ ሥቃይም ከዚህ ዓለም በሞት ይለያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕድሜያቸውንም በተድላ ይፈጽማሉ፥ ድንገትም ወደ ሲኦል ይወርዳሉ። |
ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል።
አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና ዐሳብ፥ ዕውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምትችለውን ሁሉ እንደ ኀይልህ አድርግ።
ከእስራኤልም ሁሉ የተመረጡ ዐሥር ሺህ ሰዎች ወደ ገባዖን አንጻር መጡ፤ ውጊያውም በርትቶ ነበር፤ መከራም እንዲያገኛቸው አላወቁም ነበር።