ኢዮብ 21:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬዎቻቸው አይመክኑም፤ ላሞቻቸውም አይጨነግፉም፤ በደኅናም ይወልዳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኰርማቸው ዘሩ በከንቱ አይወድቅም፤ ያስረግዛል፤ ላማቸውም ሳትጨነግፍ ትወልዳለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩንም አይጥለውም፥ ላማቸውም ትወልዳለች፥ አትጨነግፍም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብቶቻቸው ያለአንዳች ችግር ይረባሉ፤ ላሞቻቸውም ምንም ሳይጨነግፉ ይወልዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኮርማቸው ይወልዳል፥ ዘሩንም አይጥለውም፥ ላማቸውም ትወልዳለች፥ አትጨነግፍም። |
ቤታቸው በብልፅግና የተሞላ ነው፤ የሚያስፈራቸውም የለም። ከእግዚአብሔርም ዘንድ መቅሠፍት አይመጣባቸውም።
አምላክህ እግዚአብሔርም እርስዋን ይሰጥህ ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው በምድርህ ላይ፥ በሆድህ ፍሬ፥ በእርሻህም ፍሬ፥ ከብቶችህን በማብዛት እግዚአብሔር በጎነቱን ያበዛልሃል።