ኢዮብ 20:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጨለማ ሁሉ ይጠብቀዋል፤ ዕፍ የማይባል እሳትም ይበላዋል፤ እንግዳም ቤቱን ያጠቃዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጓል፤ ሰው ባላራገበው እሳት ይበላል፤ በድንኳኑም ውስጥ የተረፈውን ይልሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለከበሩ ዕቃዎቹ ጨለማ ተዘጋጅቶአል፥ በሰው እፍ ያልተባለች እሳት ትበላዋለች፥ በድንኳኑ ውስጥ የቀረውም ይጋያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያካበተው ንብረት ሁሉ ጥቅጥቅ ባለ ጨለማ ውስጥ ይወድማል፤ በሰው እጅ ያልተቀጣጠለ እሳትም ያቃጥለዋል፤ በቤቱ ውስጥ የሚተርፈውን ንብረት ሁሉ ያጋየዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጨለማ ሁሉ ስለ ከበረው ዕቃ ተዘጋጅቶአል፥ በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፥ በድንኳኑ ውስጥ የቀረው ይጨነቅባታል። |
ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል።
ወደ ታችም ወደ ምድር ትመለከታላችሁ፤ ድቅድቅ ጨለማንም ታያላችሁ፤ ታላቅ መከራንም ትቀበላላችሁ፤ ትጨነቃላችሁ፤ ትቸገራላችሁም፤ በፊታችሁም ጨለማ ይሆናል፤ አታዩምም፤ በመከራም ያለ ጊዜው እስኪደርስ አይድንም።