ኢዮብ 20:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሰይፍም ኀይል አያመልጥም፤ የናስም ቀስት ይወጋዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብረት መሣሪያ ቢሸሽም፣ የናስ ቀስት ይወጋዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብረት መሣሪያም ቢሸሽ፥ የናስ ቀስት ይወጋዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብረት ሰይፍ ቢያመልጥ በነሐስ ፍላጻ ይወጋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብረት መሣሪያም ይሸሻል፥ የናስም ቀስት ይወጋዋል። |
የሰማይ መስኮቶችም ተከፍተዋልና፥ የምድርም መሠረት ተናውጣለችና ከፍርሀት ድምፅ የሸሸ በገደል ይወድቃል፤ ከገደልም የወጣ በወጥመድ ይያዛል።
ከአንበሳ ፊት እንደ ሸሸ፥ ድብም እንዳገኘው ሰው፥ ወደ ቤትም ገብቶ እጁን በግድግዳ ላይ እንዳስደገፈና እባብ እንደ ነደፈው ሰው ይሆናል።