ኢዮብ 20:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የደካሞችን ቤቶች አፍርሶአልና፤ ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድኾችን በመጨቈን ባዶ አስቀርቷቸዋልና፣ ያልሠራውንም ቤት ነጥቋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድሀውን ረግጦአል፥ ትቶታልም፥ ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም የሚሆነው ድኻን ስለ ጨቈነና ያልሠራውንም ቤት በግፍ ስለ ወሰደ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሀውን አስጨንቆአል፥ ትቶታልም፥ ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል። |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አየሁ፤ እነሆም፥ የተገፉት ሰዎች እንባ ነበረ፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፉአቸውም እጅ ኀይል ነበረ። እነርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።
ከፍ ካለው በላይ ከፍ ያለ ይጠብቅሃልና፥ ከእነርሱም በላይ ደግሞ ሌሎች ከፍ ይላሉና በሀገሩ ድሃ ሲበደል፥ ፍርድና ጽድቅም ሲነጠቅ ብታይ በሥራው አታድንቅ።
ድሃውንም ደብድባችኋልና፤ መማለጃንም ከእርሱ ወስዳችኋልና፤ ያማሩ ቤቶችንም መርጣችሁ ሠርታችኋልና፥ ነገር ግን አትኖሩባቸውም፤ ያማሩ የወይን ቦታዎችም ተክላችኋል፤ ነገር ግን ወይንን አትጠጡም።
ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኀጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ ዐውቃለሁና።
የምድርህን ፍሬ፥ ድካምህንም ሁሉ የማታውቀው ሕዝብ ይበላዋል፤ አንተም ሁልጊዜ የተጨነቅህ፥ የተገፋህም ትሆናለህ።