ኢዮብ 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፤ ማሩኝ፤ ማሩኝ፤ የእግዚአብሔር እጅ ዳስሳኛለችና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ወዳጆቼ ሆይ፤ ራሩልኝ፤ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ዕዘኑልኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ራሩልኝ፥ ራሩልኝ፥ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወዳጆቼ ሆይ! የእግዚአብሔር እጅ ስለ መታኝ እባካችሁ እናንተ እዘኑልኝ! ራሩልኝም! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ወዳጆቼ ሆይ፥ ማሩኝ፥ የእግዚአብሔር እጅ መትታኛለችና ማሩኝ። |
እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
እነሆ፥ አሁን የእግዚአብሔር እጅ በአንተ ላይ ነው፤ ዕውርም ትሆናለህ፤ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” ወዲያውኑም ታወረ፤ ጨለማም ዋጠው፤ የሚመራውም ፈለገ።
አንዱ የአካል ክፍል ቢታመም ከእርሱ ጋር የአካል ክፍሎች ሁሉ ይታመማሉ፤ አንዱ የአካል ክፍል ደስ ቢለውም የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።
ከእነርሱ ጋር አብራችኋቸው እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ እስረኞችን ዐስቡ፤ መከራ የጸናባቸውንም በሥጋችሁ ከእነሱ ጋር እንዳላችሁ ሆናችሁ ዐስቡ።
እነርሱ እስኪያድጉ ድረስ ትቆያላችሁን? ስለ እነርሱስ ባል ማግባት ትተዋላችሁን? ልጆቼ ሆይ፥ እንዲህ አይደለም፣ የእግዚአብሔር እጅ በእኔ ወጥቶአልና ከእናንተ የተነሣ እጅግ ተመርሬአለሁ።