ኢዮብ 19:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍርበቴ ከሥጋዬ ጋር ይበጣጠሳል። አጥንቶቼም ይፋጩብኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቈዳና ዐጥንት ብቻ ሆኜ ቀረሁ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋዬ አልቆ ቆዳዬ በአጥንቴ ላይ ተጣበቀ፤ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ ተረፍኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ። |
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ ቍርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨትም ሆኖአል።
ከከተማችሁ የተጣበቀብንን ትቢያ እንኳን እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ እንደ ቀረበች ይህን ዕወቁ።