እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ ድንገት መጥቶ ቤቱን በአራት ማዕዘኑ መታው፥ ቤቱም በብላቴኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።”
ኢዮብ 19:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አገልጋዮችን እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱ ግን ቸል ይሉኛል፤ በአፌም እለማመጣቸዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አገልጋዬን ብጣራ፣ በአንደበቴም ብለምነው፣ አይመልስልኝም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዬን ብጠራ አይመልስልኝም፥ በአፌም መለማመጥ አለብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዬን ስጠራው መልስ አይሰጠኝም እባክህ እርዳኝ ብዬ ስለምነውም እንኳ እሺ አይለኝም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዬን ብጠራ፥ በአፌም ባቈላምጥ አይመልስልኝም። |
እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ ድንገት መጥቶ ቤቱን በአራት ማዕዘኑ መታው፥ ቤቱም በብላቴኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።”