ኢዮብ 19:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በታላቅ ቍጣም ያዘኝ እንደ ጠላትም ቈጠረኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቍጣው በላዬ ነድዷል፤ እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቁጣውንም አነደደብኝ፥ እንደ ጠላቱም ቈጠረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ተቈጥቶ መዓቱን አፈሰሰብኝ፤ እንደ ጠላትም ቈጠረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቍጣውንም አነደደብኝ፥ እንደ ጠላቱም ቈጠረኝ። |
ዳሌጥ። ቀስቱን እንደ ተቃዋሚ ጠላት ገተረ፤ እንደ ባላጋራም ቀኝ እጁን አጸና፤ በጽዮን ሴት ልጅ ድንኳን ለዐይኑ የሚያምረውን ሁሉ ገደለ፤ መዓቱንም እንደ እሳት አፈሰሰ።
ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።