ኢዮብ 17:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ናት? ዳግመኛስ መልካም ነገርን አያታለሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ የእኔ ተስፋ ወዴት ነው? ተስፋዬን የሚያይልኝስ ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እኔ ምን ተስፋ አለኝ? ተስፋ የሚሆነኝንስ ነገር ማን ያይልኛል? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ተስፋዬ ወዴት ነው? ተስፋዬንስ የሚያይ ማን ነው? |
እግዚአብሔርም ተናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።