ኢዮብ 16:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ትድረስ፥ ዐይኔም በፊቱ እንባ ታፍስስ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ለወዳጁ እንደሚማልድ፣ በእግዚአብሔር ፊት የሚማልድ ሰው ምነው በተገኘ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውና ሰውን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ እንዳለ ሁሉ፥ ምነው ሰውንና እግዚአብሔርን አወቃቅሶ የሚያስታርቅ በኖረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰው ልጅ ከባልንጀራው ጋር እንደሚምዋገት፥ ሰው በእግዚአብሔር ፊት ለመምዋገት ምነው በቻለ! |
የሚያደምጠኝን ማን በሰጠኝ! የእግዚአብሔርንም እጅ አልፈራሁ እንደ ሆነ፥ የሚያስፈርድብኝ የክስ ጽሑፍ ምነው በኖረኝ!
“እንደ ሸክላ ሠሪ ሥራ ውብ አድርጌ ሠራሁህ፤ ምድርን የሚያርስ ሁልጊዜ ያርሳልን? ጭቃ ሠሪውን፦ ምን ትሠራለህ? እጅ የለህምና መሥራት አትችልም ይለዋልን? ጭቃ ሠሪውን ይከራከረዋልን?