ኢዮብ 15:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀኑ ሳይደርስ መከሩ ይጠፋል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጊዜው ሳይደርስ ይጠወልጋል፤ ቅርንጫፉም አይለመልምም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኑ ሳይደርስ ጊዜው ይፈጸማል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጊዜው ሳይደርስ ግንዱ እንደሚደርቅና ቅርንጫፎቹም እንደማይለመልሙ ዛፍ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀኑ ሳይደርስ ጊዜው ይፈጸማል፥ ቅርንጫፉም አይለመልምም። |
ዘግይቶ ይደርቃል፤ በውስጡም ልምላሜ ሁሉ አይገኝም፤ ከቲኣሳ የምትመጡ ሴቶች፥ ኑና ለሕዝቤ አልቅሱ፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና፤ ስለዚህ ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።