ኢዮብ 15:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እርሱ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይጸናም፤ ጥላውንም በምድር ላይ አይጥልም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባለ ጠጋ አይሆንም፥ ሀብቱም አይጸናም፥ ጥላውንም በምድር ላይ አይጥልም፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለጸጋ አይሆንም፥ ሀብቱም ለብዙ ጊዜ አይቈይም፤ በምድር ላይም አይስፋፋም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባለጠጋ አይሆንም፥ ሀብቱም አይጸናም፥ ጥላውንም በምድር ላይ አይጥልም፥ |
ጌታውም ጠርቶ፦ ‘በአንተ ላይ የምሰማው ይህ ነገር ምንድን ነው? እንግዲህ ወዲህ ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ’ አለው።
ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።