ኢዮብ 15:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መከራና ጭንቀት ይመጡበታል፤ በፊት እንደ ተሰለፈ መኰንን ይወድቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጭንቀትና ሐዘን ያስፈራሩታል፤ ለማጥቃት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥም ያይሉበታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጨለማው ጊዜ አስፈራራው፤ አንድ ንጉሥ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ዐይነት ሐዘንና ጭንቀት ይበረቱበታል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መከራና ጭንቀት ያስፈራሩታል፥ ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ ያሸንፉታል። |
ለአሞራዎችም ምግብ ሆኖ ተሰጥቶአል በድን ሆኖ እንደሚቈይም እርሱ ራሱ ያውቃል። የጨለማ ቀንም እንደ አውሎ ነፋስ ትወስደዋለች።
ጭቅጭቅ ድንገት በመጣባችሁ ጊዜ፥ እንደዚሁም ጥፋታችሁ እንደ ዓውሎ ነፋስ በመጣባችሁ ጊዜ፥ ችግርና ምርኮ በደረሰባችሁ ጊዜ፥ እኔ ከዚያ አለሁ።
እንግዲህ ድህነት እንደ ክፉ መልእክተኛ፥ ችግርም እንደ ደኅና ርዋጭ ይመጣብሃል። ሰነፍ ባትሆን ግን ባለጸግነትህ እንደምንጭ ይመጣልሃል፤ ችግርም እንደ ክፉ ርዋጭ ከአንተ ይርቃል።
እኔ አዝዤ ቅዱሳኔን አመጣቸዋለሁ፤ ኀያላኔንም አመጣቸዋለሁ፤ ደስ እያላቸውም ይመጣሉ፤ ቍጣዬንም ይፈጽማሉ፤ ያዋርዱአቸዋልም።
የይሁዳንም ንጉሥ ኢዮአቄምን እንዲህ በለው፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አንተ፦ የባቢሎን ንጉሥ በርግጥ ይመጣል፤ ይችንም ሀገር ያፈርሳታል፤ ሰውና እንስሳም ያልቃሉ ብለህ ለምን ጻፍህበት? ብለህ ይህን ክርታስ አቃጥለሃል።