ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
ኢዮብ 15:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምድር ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታለችና፤ በመካከላቸውም እንግዳ ሕዝብ አልገባባቸውምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድሪቱ ለአባቶቻቸው ተሰጠች፤ በመካከላቸውም ባዕድ አልተቀመጠም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታለችና፥ በመካከላቸውም እንግዳ አልገባባቸውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድሪቱ ለእነርሱ ብቻ ተሰጥታ ነበር፤ መጻተኞችም በመካከላቸው አልተቀላቀሉባቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመካከላቸውም እንግዳ ያልገባባቸው ጠቢባን ከአባቶቻቸው ተቀብለው የተናገሩትን ያልሸሸጉትንም፥ እገልጥልሃለሁ፥ ስማኝ፥ ያየሁትንም እነግርሃለሁ። |
ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፤ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው።
የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። ከእነዚህም ከጥፋት ውኃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ ተዘሩ።
“እኔም በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።
ልዑል አሕዛብን በከፈላቸው ጊዜ፥ የአዳምንም ልጆች በለያቸው ጊዜ፥ እንደ እግዚአብሔር መላእክት ቍጥር፥ አሕዛብን በየድንበራቸው አቆማቸው።