ኢዮብ 14:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጆቹ ቢበዙ አያያቸውም ቢያንሱም አያውቃቸውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጆቹ ቢከበሩ አያውቅም፤ ቢዋረዱም አያይም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፥ ቢዋረዱም አያይም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቹ ክብር ቢያገኙ አያውቅም፤ ቢዋረዱም አያይም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልጆቹ ቢከብሩ አያውቅም፥ ቢዋረዱም አያይም። |
ከፍ ከፍ ባለ ጊዜም ብዙዎችን አስጨነቃቸው። እንደ አመድማዶ በሙቀት ይጠወልጋል። ከቃርሚያው እንደሚወድቅ እሸትም ይቈረጣል።
መሥዋዕትንና ቍርባንን አልወደድሁም፤ ሥጋህን አንጻልኝ፤ የሚቃጠለውንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልወደድሁም።
ሕያዋን እንዲሞቱ ያውቃሉና፤ ሙታን ግን አንዳች አያውቁም፤ መታሰቢያቸውም ተረስቶአልና ከዚህ በኋላ ዋጋ የላቸውም።
አንተ አባታችን ነህ፤ አብርሃም ግን አላወቀንም፤ እስራኤልም አልተገነዘበንም፤ ነገር ግን አንተ አባታችን አድነን፤ ስምህም ለዘለዓለም በእኛ ላይ ነው።
ወደ ሞትም በቀረበች ጊዜ በዙሪያዋ ያሉት ሴቶች “ወንድ ልጅ ወልደሻልና አትፍሪ” አሉአት። እርስዋ ግን አልመለሰችላቸውም፤ ልብዋም አያስታውስም ነበር።