ሰው የሕይወቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕይወት የሚኖር ቢሆን ዳግመኛ እስክወለድ ድረስ፥ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
ኢዮብ 14:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዘለዓለም ታስወግደዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፤ ፊትህን ትመልስበታለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዘለዓለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥ ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይልህ ለዘለዓለም በእርሱ ላይ ይበረታል፤ እርሱም እንዳልነበረ ይሆናል፤ መልኩንም ለውጠህ ከፊትህ ታስወግደዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዘላለም ታሸንፈዋለህ፥ እርሱም ያልፋል፥ ፊቱን ትለውጣለህ፥ እርሱንም ትሰድደዋለህ። |
ሰው የሕይወቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕይወት የሚኖር ቢሆን ዳግመኛ እስክወለድ ድረስ፥ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
ከሩቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላወቁትም፤ በታላቅ ድምፅም ጮኸው አለቀሱ፤ መጐናጸፊያቸውንም ቀደዱ፥ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ።
መንፈስን ለማስቀረት በመንፈሱ ላይ ሥልጣን ያለው ሰው የለም፤ በሞትም ቀን ሥልጣን የለውም፤ በጦርነትም ጊዜ ስንብት የለም፥ ኀጢአትም ሠሪውን አያድነውም።
ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቍሮአል፤ በመንገድም አልታወቁም፤ ቍርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፤ ደርቆአል፤ እንደ እንጨትም ሆኖአል።