እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
ኢዮብ 14:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ውኆች ድንጋዮችን ይፍቃሉ፤ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፤ እንዲሁ አንተ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ ጐርፍም ዐፈርን ዐጥቦ እንደሚወስድ፣ አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁም የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሃ ድንጋይን እየቦረቦረ እንደሚጨርስ፥ ኀይለኛ ዝናብም መሬትን እንደሚሸረሽር፥ አንተም እንዲሁ የደካማን ሰው ተስፋ ታጠፋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ውኆች ድንጋዮቹን ይፍቃሉ፥ ፈሳሾቹም የምድሩን አፈር ይወስዳሉ፥ እንዲሁ የሰውን ተስፋ ታጠፋዋለህ። |
እኔም እነሆ፥ ከሰማይ በታች የሕይወት ነፍስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፤ በምድር ያለው ሁሉ ይጠፋል።
እግዚአብሔርም ተናገረኝ፤ እንዲህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነዚህ አጥንቶች የእስራኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥንቶቻችን ደርቀዋል፤ ተስፋችንም ጠፍቶአል፤ ፈጽመንም ተቈርጠናል ብለዋል።