ኢዮብ 14:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠራኸኝም ጊዜ በመለስሁልህ ነበር፤ የእጅህንም ሥራ አትናቀኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፥ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ አንተ ትጠራኛለህ፤ እኔም ‘አቤት’ እልሃለሁ፤ ፍጡርህ የሆንኩትን እኔን ለማየት ትናፍቃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠራኸኝና በመለስሁልህ ነበር፥ የእጅህንም ሥራ በተመኘኸው ነበር። |
ሰው የሕይወቱን ዘመን ፈጽሞ ከሞተ በኋላ በሕይወት የሚኖር ቢሆን ዳግመኛ እስክወለድ ድረስ፥ በትዕግሥት በተጠባበቅሁ ነበር።
ስለ ምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኀጢአቴንስ ስለ ምን አታነጻም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፤ በማለዳም አልነቃም።”
ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።