La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነሆ፥ ኀያሉ እጁን በእኔ ላይ ቢጭን፥ እርሱ እንደ ጀመረ እና​ገ​ራ​ለሁ፥ በፊ​ቱም እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቢገድለኝም እንኳ በርሱ ተስፋ አደርጋለሁ፤ ስለ መንገዴም ፊት ለፊት እከራከረዋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነሆ፥ ሊገድለኝ ይችላል፥ ተስፋም ባይኖረኝ፥ ነገር ግን ስለ መንገዴ በፊቱ እሟገታለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ እግዚአብሔር ሊገድለኝ ቢፈልግ ምንም የሚቀርብኝ ነገር የለም፤ ሆኖም ሁኔታዬን ለእርሱ አስረዳለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነሆ፥ ቢገድለኝ ስንኳ እርሱን በትዕግሥት እጠባበቃለሁ፥ ነገር ግን መንገዴን በፊቱ አጸናለሁ።

Ver Capítulo



ኢዮብ 13:15
20 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በላይ በደ​ለኛ እን​ዳ​ል​ሆ​ንሁ፥ አንተ ታው​ቃ​ለህ። ነግር ግን ከእ​ጅህ የሚ​ያ​መ​ልጥ ማን ነው?


እነሆ፥ ወደ ፍርዴ ቀር​ቤ​አ​ለሁ። ጽድ​ቄም እን​ደ​ም​ት​ገ​ለጥ አው​ቃ​ለሁ።


ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እና​ገ​ራ​ለሁ፤ ከፈ​ቀ​ደም በፊቱ እዋ​ቀ​ሳ​ለሁ።


ሆዴ በል​ቅሶ ተቃ​ጠለ፤ የሞት ጥላን በቅ​ን​ድ​ቦች ላይ አያ​ለሁ፤


ጸሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትድ​ረስ፥ ዐይ​ኔም በፊቱ እንባ ታፍ​ስስ።


መን​ገ​ዴን ፈጽሞ ዐወቀ፥ እንደ ወር​ቅም ፈተ​ነኝ


እና​ን​ተን ማጽ​ደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስ​ክ​ሞ​ትም ድረስ ፍጹ​ም​ነ​ቴን ከእኔ አላ​ር​ቅ​ምና።


“በውኑ የሚ​ከ​ራ​ከር ሰው ሁሉን ከሚ​ችል አም​ላክ ጋር ይከ​ራ​ከ​ራ​ልን? ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር የሚ​ዋ​ቀስ እርሱ ይመ​ል​ስ​ለት።”


ወይም ፍር​ዴን መቃ​ወ​ም​ህን ተው፥ ጽድ​ቅህ እን​ድ​ት​ገ​ለጥ እንጂ እኔ በሌላ መን​ገድ የም​ፈ​ር​ድ​ብህ ይመ​ስ​ል​ሃ​ልን?


ሕይ​ወቴ እንደ ሸማኔ መወ​ር​ወ​ርያ፥ ቀላል ሆነች በከ​ንቱ ተስ​ፋም ጠፋሁ።


ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆ​ቹም የነጹ፥ በነ​ፍሱ ላይ ከን​ቱን ያል​ወ​ሰደ፥ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም በሽ​ን​ገላ ያል​ማለ።


ኃጥእ በክፋቱ ይወገዳል፤ በቸርነቱ የሚታመን ግን ጻድቅ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዮና​ስን ይው​ጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አን​በ​ሪን አዘዘ፤ ዮና​ስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አን​በ​ሪው ሆድ ውስጥ ነበረ።


እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፣ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።