ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእስራኤል ሀገር ነቢዩ ኤልሳዕ ያለ አይደለምን? በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውንና ቃልህን ሁሉ ለእስራኤል ንጉሥ እርሱ ይነግረዋል፤” አለ።
ኢዮብ 12:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥልቅ ነገርን ከጨለማ ይገልጣል፤ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል፤ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጨለማ ውስጥ ጥልቅን ነገር ይገልጣል፥ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ይለውጣል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ይገልጣል፤ ድቅድቅ ጨለማን ወደ ብርሃን ይለውጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጥልቅ ነገር ከጨለማ ይገልጣል፥ የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል። |
ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእስራኤል ሀገር ነቢዩ ኤልሳዕ ያለ አይደለምን? በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውንና ቃልህን ሁሉ ለእስራኤል ንጉሥ እርሱ ይነግረዋል፤” አለ።
የጥበቡን ኀይል ቢገልጥልህ! ባንተ ላይ ያለው እጥፍ ነውና። ያንጊዜም ከእግዚአብሔር ዘንድ በበደልህ ያገኘህ ትክክል እንደ ሆነ ታውቃለህ።
ሁሉን የሚሠራና የሚያቅናና፥ ብርሃኑን ወደ መስዕ የሚመልሰው፥ ቀኑን እንደ ሌሊት የሚያጨልመው፥ የባሕሩንም ውኃ ጠርቶ በምድር ፊት የሚያፈስሰው ስሙ ሁሉን የሚችል ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ጊዜው ሳይደርስ ዛሬ ለምን ትመረምራላቸሁ? በጨለማ ውስጥ የተሰወረውንም የሚያበራ፥ የልብን አሳብም የሚገልጥ ጌታችን ይመጣል፤ ያንጊዜ ሁሉም ዋጋውን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል።