ኢዮብ 12:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መካሮችንም እንዲማረኩ ያደርጋቸዋል፤ የምድር ፈራጆችንም አላዋቆች ያደርጋቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማካሪዎችንም እራቁታቸውን ይሰዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ሞኝ ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አማካሪዎችን ጥበብ ይነሣቸዋል፤ የሕዝብ መሪዎችንም ሞኞች ያደርጋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መካሮችንም እንደ ዘረፋ ይወስዳቸዋል፥ ፈራጆችንም ያሳብዳል። |
አቤሴሎምና የእስራኤልም ሰዎች ሁሉ “የአርካዊው የኩሲ ምክር ከአኪጢፌል ምክር ይሻላል” አሉ። እግዚአብሔርም በአቤሴሎም ላይ ክፉ ያመጣ ዘንድ እግዚአብሔር መልካሚቱን የአኪጦፌልን ምክር እንዲበትን አዘዘ።
አኪጦፌልም ምክሩ እንዳልሠራ ባየ ጊዜ አህያውን ጫነ፤ ተነሥቶም ወደ ቤቱ ወደ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አደራጅቶ በገዛ እጁ ታንቆ ሞተ፤ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።
ስለዚህ፥ እነሆ፥ ይህ ሕዝብ በድጋሚ እንዲፈልስ አደርጋለሁ፤ አፈልሳቸዋለሁም፤ የጥበበኞችንም ጥበብ አጠፋለሁ፤ የአስተዋዮችንም ማስተዋል እሰውራለሁ።”