La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢዮብ 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማራ​ኪ​ዎ​ችም መጥ​ተው ወሰ​ዱ​አ​ቸው፥ ብላ​ቴ​ኖ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሳባውያን ጥቃት አድርሰውባቸው ይዘዋቸው ሄዱ፤ አገልጋዮቹንም በሰይፍ ገደሉ። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሳባ ሰዎች አደጋ ጣሉና ወሰዱአቸው፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የሳባ ሰዎች መጥተው አደጋ በመጣል ሁሉንም ዘርፈው ወሰዱ፤ አገልጋዮችህን ሁሉ በሰይፍ ገደሉአቸው፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሳባም ሰዎች አደጋ ጣሉ፥ ወሰዱአቸውም፥ ብላቴኖቹንም በሰይፍ ስለት ገደሉ፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው።

Ver Capítulo



ኢዮብ 1:15
13 Referencias Cruzadas  

ዖባ​ል​ንም፥ አቤ​ማ​ኤ​ል​ንም፥ ሳባ​ንም፥


የኩ​ሽም ልጆች ሳባ፥ ኤው​ላጥ፥ ሰብታ፥ ሬጌም፥ ሰበ​ቅታ ናቸው። የሬ​ጌም ልጆ​ችም ሳባ፥ ዮድ​ዳን ናቸው።


ዮቃ​ጤ​ንም ሶቤ​ቅን፥ ቲማ​ን​ንና ድዳ​ንን ወለደ። የድ​ዳ​ንም ልጆች ራጉ​ኤል፥ ንበ​ከዝ፥ እስ​ራ​ኦ​ምና ሎአም ናቸው።


መል​እ​ክ​ተ​ኛም ወደ ኢዮብ መጥቶ፥ “ጥምድ በሬ​ዎ​ችህ እርሻ ያርሱ ነበር፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም ሴቶች አህ​ዮ​ችህ ይሰ​ማሩ ነበር፤


እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከም​ድረ በዳ ድን​ገት መጥቶ ቤቱን በአ​ራት ማዕ​ዘኑ መታው፥ ቤቱም በብ​ላ​ቴ​ኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነ​ር​ሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻ​ዬን አም​ልጬ እነ​ግ​ርህ ዘንድ መጣሁ።”


የቴ​ማ​ና​ው​ያ​ንን መን​ገ​ዶች፥ የሳ​ባ​ው​ያ​ንን ክፋ​ትና ቸል​ተ​ኝ​ነት ተመ​ል​ከቱ።


ስለ​ዚህ ሕዝቤ ወደ​ዚህ ይመ​ለ​ሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላ​ያ​ቸው ይገ​ኛል፤


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ግብ​ፅና የኢ​ት​ዮ​ጵያ ንግ​ዶች ደከሙ፤ ቁመተ ረዥ​ሞች የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም ይገ​ዙ​ል​ሃል፤ እጆ​ቻ​ቸ​ውን ታስ​ረው በኋ​ላህ ይከ​ተ​ሉ​ሃል፤ በፊ​ት​ህም ያል​ፋሉ፤ ለአ​ን​ተም እየ​ሰ​ገዱ፦ በእ​ው​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ ከእ​ር​ሱም ሌላ አም​ላክ የለም ብለው ይለ​ም​ኑ​ሃል።


የበ​ገ​ና​ውን አው​ታር ድምፅ ይቃ​ኛሉ፤ ከብዙ ሰዎ​ችም ጉባኤ ጋር ሰካ​ራ​ሞቹ ከም​ድረ በዳ መጡ፤ በእ​ጃ​ቸው አን​ባር፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም የተ​ዋበ አክ​ሊል አደ​ረጉ።


በዚያ ቀን ያመ​ለ​ጠው ይህን ነገር በጆ​ሮህ ያሰማ ዘንድ ወደ አንተ ይመ​ጣል።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን በይ​ሁዳ ልጆች እጅ እሸ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ለሩ​ቆቹ ሕዝብ በም​ርኮ ይሸ​ጡ​አ​ች​ኋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።