ኢሳይያስ 63:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ፥ በቀላይ ውስጥ አሳለፋቸው፥ እነርሱም አልደከሙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈረስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ ሁሉ፣ እነርሱንም በጥልቁ ውስጥ አሳልፎ መራቸው፤ ስለዚህም አልተሰናከሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፥ በቀላይ ውስጥ ያለ እንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጥልቁ ሲሄዱ እንዳይሰናከሉ ለጥ ባለ ሜዳ ላይ እንዳለ ፈረስ አደረጋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድረ በዳም እንደሚያልፍ ፈረስ፥ በቀላይ ውስጥ ያለ እንቅፋት ያሳለፋቸው ወዴት ነው ያለ? |
ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የአዜብ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው፤ ባሕሩንም አደረቀው፤ ውኃውም ተከፈለ።
እያለቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስሄዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።”
ዳግመኛም የአሕዛብን ስድብ አላሰማብሽም፤ ዳግመኛም የአሕዛብን ውርደት አትሸከሚም፤ ዳግመኛም ሕዝብሽን አታሰናክዪም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”