ተኵላዎችም በዚያ ያድራሉ፤ ቀበሮዎችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይዋለዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆናል፤ አይዘገይምም።
ኢሳይያስ 35:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደረቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተጠማች ምድርም የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ የዎፎች መኖሪያም ሸንበቆና ደንገል ይሆንበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንዳዳማው ምድር ኵሬ ይሆናል፤ የተጠማው መሬት ውሃ ያመነጫል። ቀበሮዎች በተኙባቸው ጕድጓዶች፣ ሣር፣ ሸንበቆና ደንገል ይበቅልበታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደረቂቱ ምድር ኩሬ፥ የተጠማች መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፤ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ለምለም፥ ሸምበቆው ደንገል ይበቅልበታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚያቃጥለው አሸዋ ኩሬ ይሆናል፤ ደረቁም ምድር በምንጭ ውሃ ይረሰርሳል፤ የቀበሮዎች መፈንጫ የነበረው ስፍራ ለምለም ሣርና ቄጠማ የሚበቅልበት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደረቂቱ ምድር ኵሬ፥ የጥማት መሬት የውኃ ምንጭ ትሆናለች፥ ቀበሮ የተኛበት መኖሪያ ልምላሜና ሸምበቆው ደንገልም ይሆንበታል። |
ተኵላዎችም በዚያ ያድራሉ፤ ቀበሮዎችም በሚያማምሩ አዳራሾቻቸው ይዋለዳሉ፤ ይህም ሁሉ ፈጥኖ ይሆናል፤ አይዘገይምም።
በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ፥ በረዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።
በተራሮች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፥ የተጠማችውንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
የምድረ በዳ አራዊት፥ ቀበሮችና ሰጎኖች፥ ያከብሩኛል። የመረጥሁትን ሕዝቤን አጠጣ ዘንድ በምድረ በዳ ውኃን፥ በበረሃም ወንዞችን ሰጥቻለሁና፤
በምድረ በዳም በተጠሙ ጊዜ፥ ውኃን ከዓለቱ ውስጥ ያፈልቅላቸው ነበር፤ ዓለቱም ተሰነጠቀ፤ ውኃውም ይፈስስላቸው ነበር፤ ሕዝቤም ይጠጡ ነበር።
የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም።
እርሱም እንዲህ አለኝ፥ “ይህ ውኃ ወደ ምሥራቅ ወደ ገሊላ ይወጣል፤ ወደ ዓረባም ይወርዳል፤ ወደ ባሕሩም ይገባል፤ ወደ ባሕሩም ወደ ረከሰው ውኃ በገባ ጊዜ ውኃውን ይፈውሰዋል።
እኔ ከምሰጠው ውኃ የሚጠጣ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውኃ በውስጡ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውኃ ምንጭ ይሆንለታል እንጂ።”
ይኸውም ዐይናቸውን ትከፍትላቸው ዘንድ፥ ከጨለማም ወደ ብርሃን፥ ሰይጣንን ከማምለክም ወደ እግዚአብሔር ትመልሳቸው ዘንድ፥ ኀጢአታቸውም ይሰረይላቸው ዘንድ፥ በስሜም በማመን ከቅዱሳን ጋር አንድነትን ያገኙ ዘንድ ነው።’
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤