La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 33:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለእ​ና​ንተ ታላቅ ነው፤ ሀገ​ራ​ች​ሁም የሰፉ ወን​ዞ​ችና ታላቅ የመ​ስኖ ስፍራ ይሆ​ናል፤ በዚ​ህች መን​ገድ አት​ሄ​ድም፤ መር​ከ​ቦ​ችም አይ​ሄ​ዱም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር በዚያ ኀይላችን ይሆናል፤ ባለመቅዘፊያ ጀልባዎች እንደማያልፉባቸው፣ ታላላቅ መርከቦችም እንደማይሻገሯቸው፣ ሰፋፊ ወንዞችና ጅረቶች ይሆንልናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ግን በእነዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ በግርማ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፤ ታላላቅ መርከቦች አያልፉባትም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እዚያም ማንም ጀልባዎችን በማይቀዝፍባቸውና ትላልቅ መርከቦች በማይንሳፈፉባቸው በወንዞችና በሰፋፊ ጅረቶች እግዚአብሔር በታላቅ ግርማው ከእኛ ጋር ይሆናል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል፥ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፥ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 33:21
14 Referencias Cruzadas  

አቤቱ፥ ነፍ​ሴን ከሲ​ኦል አወ​ጣ​ሃት፥ ወደ ጕድ​ጓ​ድም ከሚ​ወ​ር​ዱት ለይ​ተህ አዳ​ን​ኸኝ።


አንቺ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ ሐሤ​ትም አድ​ርጊ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ በመ​ካ​ከ​ልሽ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና።”


ንጉ​ሥን በክ​ብሩ ታዩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በሩቅ ያለች ምድ​ርን ያዩ​አ​ታል።


በተ​ራ​ሮች ላይ ወን​ዞ​ችን፥ በሸ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ምን​ጮ​ችን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መቆ​ሚያ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ው​ንም ምድር ለውኃ መፍ​ለ​ቂያ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


የም​ድረ በዳ አራ​ዊት፥ ቀበ​ሮ​ችና ሰጎ​ኖች፥ ያከ​ብ​ሩ​ኛል። የመ​ረ​ጥ​ሁ​ትን ሕዝ​ቤን አጠጣ ዘንድ በም​ድረ በዳ ውኃን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን ሰጥ​ቻ​ለ​ሁና፤


ትእ​ዛ​ዜን ብት​ሰማ ኖሮ፥ ሰላ​ምህ እንደ ወንዝ ጽድ​ቅ​ህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ፥ ሰላ​ምን እንደ ወንዝ፥ የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ክብር እን​ደ​ሚ​ጐ​ርፍ ፈሳሽ እመ​ል​ስ​ላ​ታ​ለሁ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል፤ በጕ​ል​በ​ታ​ቸ​ውም ላይ እያ​ስ​ቀ​መጡ ያቀ​ማ​ጥ​ሏ​ቸ​ዋል።


እነሆ፥ እጄን በላያቸው አወዛውዛለሁ፥ ተገዝተው ለነበሩት ብዝበዛ ይሆናሉ፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


በያ​ዕ​ቆብ ላይ ድካም የለም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕማም አይ​ታ​ይም፤ አም​ላኩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ርሱ ጋር ነው፤ የአ​ለ​ቆ​ችም ክብር ለእ​ርሱ ነው።


እር​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንና አባ​ቶ​ቻ​ችን ሆይ፥ ስሙ፤ የክ​ብር አም​ላክ ለአ​ባ​ታ​ችን ለአ​ብ​ር​ሃም በሁ​ለት ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ወደ ካራ​ንም ሳይ​መጣ ተገ​ለ​ጠ​ለት።


“ከጌ​ታዉ ኰብ​ልሎ ወደ አንተ የተ​ጠ​ጋ​ውን ባሪያ ለጌ​ታው አሳ​ል​ፈህ አት​ስጥ።