ኢሳይያስ 33:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ የመድኀኒታችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህም ድንኳኖችዋ የማይናወጡ፥ ካስማዎችዋ ለዘለዓለም የማይነቀሉ፥ አውታሮችዋም ሁሉ የማይበጠሱ፥ የበለጸገች ከተማ ኢየሩሳሌምን ያያሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓላታችንን የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ሰላማዊ መኖሪያ፣ የማትነቃነቅ ድንኳን የሆነችውን፣ ካስማዋ የማይነቀል፣ ከገመዷ አንዱ እንኳ የማይበጠሰውን፣ ኢየሩሳሌምን ዐይኖችህ ያያሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ የማይወገድ ድንኳን፥ ካስማውም ለዘለዓለም የማይነቀል፥ አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታወቁ የሃይማኖት በዓላትን የምናከብርባትን የጽዮንን ከተማ ተመልከቱ፤ በሰላም ትኖሩባት ዘንድ ምቹ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን እዩ! ካስማዎቹ ከቶ እንደማይነቀሉ፥ ገመዶቹም እንደማይበጠሱና ከስፍራው እንደማይንቀሳቀስ ድንኳን ትሆናለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የባዓላችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፥ ዓይኖችህ የሰላም ማደሪያ፥ ካስማውም ለዘላለም የማይነቀል አውታሩም ሁሉ የማይበጠስ፥ የማይወገድ ድንኳን የሆነውን ኢየሩሳሌምን ያያሉ። |
በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።
ስለዚህም እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ወደዚች ከተማ አይመጣም፤ ፍላጻንም አይወረውርባትም፤ በጋሻም አይመጣባትም፥ አያጥራትምም።
እግዚአብሔርም ይመጣል፤ በጽዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙሪያውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌሊትም እንደሚቃጠል የእሳት ብርሃን ይጋርዳል፤ በክብርም ሁሉ ላይ መጋረጃ ይሆናል።
የድንኳንሽን ስፍራ አስፊ፤ መጋረጃዎችሽንም ዘርጊ፤ አትቈጥቢ፤ አውታሮችሽን አስረዝሚ፤ ካስሞችሽንም ትከዪ።
ታያላችሁ፤ ልባችሁም ሐሤት ታደርጋለች፤ አጥንታችሁም እንደ ለምለም ሣር ትበቅላለች፤ የእግዚአብሔርም እጅ ለሚፈሩት ትታወቃለች፤ ዐላውያንንም ያጠፋቸዋል።”
ዙሪያዋም ዐሥራ ስምንት ሺህ ክንድ ይሆናል፥ ከዚያም ቀን ጀምሮ የከተማዪቱ ስም፦ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ተብሎ ይጠራል።”
“ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የተለየ ክፍል ይሆናል፤ ወርዱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።
ነገር ግን አምላካችሁ እግዚአብሔር ከከተሞቻችሁ ሁሉ በአንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመረጠውን ስፍራ ትሻላችሁ፤ ወደዚያም ትመጣላችሁ።
በዓመት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰባቱ ሱባዔም በዓል፥ በዳስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት እግዚአብሔር በመረጠው ስፍራ ይታይ፤
ድል የነሣው በአምላኬ መቅደስ ዓምድ እንዲሆን አደርገዋለሁ፤ ወደ ፊትም ከዚያ ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም፥ ማለት ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደውን አዲሲቱን ኢየሩሳሌምን፥ አዲሱንም ስሜን በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።