ኢሳይያስ 33:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማታውቋቸውን አሕዛብ አመጣባችኋለሁ፤ እናንት ዐማፅያን ሕዝብ፥ ጥልቅ ነገርን ትሰማላችሁ። የሚሰማም ማስተዋል እንደሌለው ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚያ ንግግራቸው የማይገባ፣ የሚሉትም የማይታወቅ፣ ሊረዱት የማይቻል ቋንቋ የሚናገሩትን ጋጠወጥ ሕዝብ ከእንግዲህ አታያቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእንግዲህ ወዲህ ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል የማይገባ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ አታይም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ልታስተውሉትና ልትረዱት በማትችሉት ቋንቋ የሚንተባተቡባችሁን እብሪተኞች ባዕዳን ሕዝቦችን ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል ጥልቅ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ፥ አታይም። |
እንደዚህ አይደለምን? እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፥ “ወደዚች ከተማ አይገባም፥ ፍላጻንም አይወረውርባትም፤ በጋሻም አይመጣባትም፥ የአፈርንም ድልድል አይደለድልባትም።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
የእስራኤል ቤት ሆይ! እነሆ ሕዝብን ከሩቅ አመጣባችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ኀያል ጥንታዊ ሕዝብ ነው፤ ቋንቋቸውንም የማታውቀው፥ የሚናገሩትንም የማታስተውለው ሕዝብ ነው።
በኦሪትም፥ “ይህን ሕዝብ በሌሎች ቋንቋዎችና በሌላ አንደበት እናገራቸዋለሁ፤ እንዲሁም ሆኖ አይሰሙኝም ይላል እግዚአብሔር” ብሎአል።