ኢሳይያስ 30:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፤ ለንጉሥም ተበጅታለች፤ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፤ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፤ የጌታም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቀድሞም ጀምሮ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅታለች፥ ለንጉሥም ተበጅታለች፥ ጥልቅና ሰፊም አድርጎአታል፥ እሳትና ብዙ ማገዶ ተከምሮአል፥ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ዲን ፈሳሽ ያቃጥለዋል። |
ሰው ሁሉ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን ለሞሎክ በእሳት እንዲሠዋ በሄኖም ልጅ ሸለቆ ቆሞ የነበረውን ጣፌትን ርኩስ አደረገው።
ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድርም የዋሆች በቅንነት ይበይናል፤ በአፉም ቃል ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ኀጢአተኛውን ያጠፋዋል።
ዓለትም ትውጣቸዋለች ድልም ይሆናሉ የሸሸም ይያዛል። በጽዮን ዘርእ፥ በኢየሩሳሌምም ቤቶች ያሉት ብፁዕ ነው” ይላል እግዚአብሔር።
በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው?
ሸለቆዎችዋ ዝፍት ሆነው ይወጣሉ፤ አፈርዋም ዲን ይሆናል፤ መሬቷም በቀንና በሌሊት እንደ ዝፍት ይቃጠላል፤ ለዘለዓለምም አይጠፋም፤
በአምላኩም በናሳራክ ቤት ሲሰግድ ልጆቹ አድራሜሌክና ሳራሳር በሰይፍ ገደሉት፤ ወደ አራራትም ሀገር ኰበለሉ። ልጁም አስራዶን በእርሱ ፋንታ ነገሠ።
እነሆ፥ እግዚአብሔር መዓቱን በቍጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ እንደ እሳት ይመጣል፤ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።
ስለዚህ እነሆ ይህ ስፍራ የእርድ ሸለቆ ይባላል እንጂ ቶፌት ወይም የሄኖም ልጅ ሸለቆ ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር።
እናንተም የይሁዳ ሰዎች በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስለ ሥራችሁ ክፋት ቍጣዬ እንደ እሳት እንዳይወጣ የሚያጠፋውም ሳይኖር እንዳይነድ ለአምላካችሁ ተገረዙ፤ የልባችሁንም ሸለፈት አስወግዱ።
ቍጣዬንም አፈስስብሃለሁ፤ በመዓቴም እሳት አናፋብሃለሁ፤ ማጥፋትንም ለሚያውቁ ለጨካኞች ሰዎች እጅ አሳልፌ እሰጥሃለሁ።
እርሱንም ሳታዩት ትወዱታላችሁ፤ አሁንም ምንም ባታዩት በእርሱ አምናችሁ፥ የእምነታችሁን ፍፃሜ እርሱም የነፍሳችሁን መዳን እየተቀበላችሁ፥ በማይነገርና ክብር በሞላበት ሐሤት ደስ ይላችኋል።
ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።