እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
ኢሳይያስ 29:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፤ የሚያጕረመርሙም መታዘዝን ይማራሉ፤ ዲዳ አንደበትም ሰላም መናገርን ይማራል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንፈስ የሳቱ ያስተውላሉ፤ የሚያጕረመርሙም ምክር ይቀበላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንፈስም የሳቱ ወደ ማስተዋል ይደርሳሉ፤ የሚያጉረመርሙም ምክርን ይቀበላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመንፈስም የሚሳሳቱ ማስተዋልን ይገበያሉ፤ ዘወትር የሚያጒረመርሙ ትምህርትን ይቀበላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ። በመንፈስም የሳቱ ማስተዋልን ያውቃሉ፥ የሚያጕረመርሙ ትምህርትን ይቀበላሉ። |
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ።
ይኸውም የእግዚአብሔር እጅ ይህን ሁሉ እንደ ሠራ፥ የእስራኤልም ቅዱስ ይህን እንደ አሳየ ያውቁ ዘንድ፥ ያስተውሉም ዘንድ፥ ይረዱም ዘንድ፥ ያምኑም ዘንድ ነው።
የአሕዛብንም ወተት ትጠጫለሽ፤ የነገሥታትንም ብልጽግና ትበያለሽ፤ እኔም እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ፥ መድኀኒትሽና ታዳጊሽ እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ።
እያንዳንዱ ሰው ባልንጀራውን፥ እያንዳንዱም ወንድሙን፦ እግዚአብሔርን ዕወቅ ብሎ አያስተምርም፤ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ያውቁኛልና፥ ይላል እግዚአብሔር። በደላቸውን እምራቸዋለሁና፥ ኀጢአታቸውንም ከእንግዲህ ወዲህ አላስብምና።”
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
ስለዚህም እልሃለሁ፤ ብዙ ኀጢኣቷ ተሰርዮላታል፤ በብዙ ወድዳለችና፤ ጥቂት የሚወድድ ጥቂት ይሰረይለታል፤ ብዙ የሚወድድም ብዙ ይሰረይለታል።”
ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው።
የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢየሩሳሌምም ምእመናን እጅግ በዙ፤ ከካህናትም መካከል ያመኑ ብዙዎች ነበሩ።
እንግዲህ እናንተ እንዲህ ስትሆኑ እነማን ናችሁ? ነገር ግን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም በአምላካችንም መንፈስ ታጥባችኋል፤ ተቀድሳችኋል፤ ጸድቃችኋልም።