La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 29:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ብ​ር​ሃም ስለ ለየው ስለ ያዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ ይላል፥ “ያዕ​ቆብ አሁን አታ​ፍ​ርም፤ ፊት​ህም አሁን አይ​ለ​ወ​ጥም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠው እግዚአብሔር ለያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፤ “ያዕቆብ ከእንግዲህ ወዲያ አያፍርም፤ ፊቱም ከእንግዲህ አይለዋወጥም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ ጌታ ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ አብርሃምን ከችግሩ ያዳነ እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቤ ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ውርደትና ኀፍረት አይደርስባችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ አብርሃምን የተቤዠ እግዚአብሔር ስለ ያዕቆብ ቤት እንዲህ ይላል፦ ያዕቆብ አሁን አያፍርም፥ ፊቱም አሁን አይለወጥም።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 29:22
29 Referencias Cruzadas  

ከከፉ ነገር ሁሉ የአ​ዳ​ነኝ መል​አክ እርሱ እነ​ዚ​ህን ብላ​ቴ​ኖች ይባ​ርክ፤ ስሜም፥ የአ​ባ​ቶች የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የይ​ስ​ሐ​ቅም ስም በእ​ነ​ርሱ ይጠራ፤ በም​ድር ላይ ይብዙ፤ የብዙ ብዙም ይሁኑ፤”


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን በዘ​ለ​ዓ​ለ​ማዊ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ እና​ን​ተም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አታ​ፍ​ሩ​ምና አቷ​ረ​ዱም።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ዘር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይጸ​ድ​ቃሉ፤ ይከ​ብ​ራ​ሉም ይባ​ላል።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳኝ፤ ስለ​ዚ​ህም አላ​ፈ​ር​ሁም፤ ፊቴ​ንም እንደ ባል​ጩት ድን​ጋይ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለሁ፤ እን​ዳ​ላ​ፍ​ርም አው​ቃ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።


ወደ አባ​ታ​ችሁ ወደ አብ​ር​ሃም፥ ወደ ወለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ወደ ሳራ ተመ​ል​ከቱ፤ አንድ ብቻ​ውን በሆነ ጊዜ ጠራ​ሁት፤ ባረ​ክ​ሁ​ትም፤ ወደ​ድ​ሁ​ትም፤ አበ​ዛ​ሁ​ትም።


አታ​ፍ​ሪ​ምና አት​ፍሪ፤ አቷ​ረ​ጂ​ምና አት​ደ​ን​ግጪ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም እፍ​ረ​ት​ሽ​ንም ትረ​ሺ​ዋ​ለሽ፤ የመ​በ​ለ​ት​ነ​ት​ሽ​ንም ስድብ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አታ​ስ​ቢም።


አንተ አባ​ታ​ችን ነህ፤ አብ​ር​ሃም ግን አላ​ወ​ቀ​ንም፤ እስ​ራ​ኤ​ልም አል​ተ​ገ​ነ​ዘ​በ​ንም፤ ነገር ግን አንተ አባ​ታ​ችን አድ​ነን፤ ስም​ህም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በእኛ ላይ ነው።


“እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከም​ርኮ ሀገር አድ​ና​ለ​ሁና ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ ያዕ​ቆ​ብም ይመ​ለ​ሳል፤ ያር​ፍ​ማል፤ ተዘ​ል​ሎም ይቀ​መ​ጣል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም።


“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል።


መቅ​ደ​ሴም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ቀ​ድ​ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ።”


“ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ አሁን የያ​ዕ​ቆ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ሁሉ እራ​ራ​ለሁ፤ ስለ ቅዱስ ስሜም እቀ​ና​ለሁ።


እኔም በእ​ስ​ራ​ኤል መካ​ከል እን​ዳ​ለሁ፥ እኔም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ፥ ከእ​ኔም በቀር ሌላ አም​ላክ እን​ደ​ሌለ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ሕዝ​ቤም ለዘ​ለ​ዓ​ለም አያ​ፍ​ርም።


“ይቅር ያለን፥ ለወ​ገ​ኖ​ቹም ድኅ​ነ​ትን ያደ​ረገ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ስ​ገን፤


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።