La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 29:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኃጥእ ሰው አል​ቆ​አ​ልና፥ ትዕ​ቢ​ተ​ኛ​ውም ጠፍ​ቶ​አ​ልና፥ በክ​ፋት የበ​ደ​ሉም ሁሉ ይነ​ቀ​ላ​ሉና፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጨካኞች እንዳልነበሩ ይሆናሉ፤ ፌዘኞችም በንነው ይጠፋሉ፤ ለክፋት ያደፈጡ ሁሉ ይወገዳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቷልና፥ ለኃጢአትም ያደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጨካኞችና ፌዘኞች ይጠፋሉ፤ ክፉ አድራጊዎችም ሁሉ ይደመሰሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጨካኙ ሰው አልቆአልና፥ ፌዘኛውም ጠፍቷልና፥ ለኃጢአትም የደፈጡ ሁሉ ይቈረጣሉና፥

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 29:20
24 Referencias Cruzadas  

የችኩል፥ የነዝናዛና የነገረኛ ሰው ስሙ ቸነፈር ነው፥ ክፉን የሚያስብም ኃጥእ ነው።


በዓ​ለም ሁሉ ላይ ክፋ​ትን አዝ​ዛ​ለሁ፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞ​ች​ንም ኀጢ​አት እጐ​በ​ኛ​ለሁ፤ የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ች​ንም ኵራት እሽ​ራ​ለሁ፤ የጨ​ካ​ኞ​ቹ​ንም ኵራት አዋ​ር​ዳ​ለሁ።


እኔ አዝዤ ቅዱ​ሳ​ኔን አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ኀያ​ላ​ኔ​ንም አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ደስ እያ​ላ​ቸ​ውም ይመ​ጣሉ፤ ቍጣ​ዬ​ንም ይፈ​ጽ​ማሉ፤ ያዋ​ር​ዱ​አ​ቸ​ዋ​ልም።


ነገር ግን የኃ​ጥ​አን ብል​ጽ​ግና እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጠ​ላ​ቶ​ች​ሽም ብዛት ነፋስ እን​ደ​ሚ​ያ​መ​ጣው ገለባ ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን እን​ዲህ ይላል፥ “በኀ​ያ​ላን የተ​ማ​ረኩ ይወ​ሰ​ዳሉ፤ የጨ​ካ​ኞ​ችም ብዝ​በዛ ያመ​ል​ጣል፤ እኔም ፍር​ድ​ሽን እፈ​ር​ድ​ል​ሻ​ለሁ፤ ልጆ​ች​ሽ​ንም አድ​ና​ለሁ።


አንቺ ግን ሰማ​ያ​ትን የፈ​ጠ​ረ​ውን፥ ምድ​ር​ንም የመ​ሠ​ረ​ታ​ትን ፈጣ​ሪ​ሽን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ረስ​ተ​ሻል፤ ያጠ​ፋሽ ዘንድ ባዘ​ጋጀ ጊዜ ከአ​ስ​ጨ​ና​ቂው ቍጣ የተ​ነሣ ሁል​ጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈር​ተ​ሻል፤ ይቈ​ጣሽ ዘንድ መክ​ሮ​አ​ልና፤ አሁን የሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቅሽ ቍጣው የት አለ?


ጽድ​ቅን የሚ​ና​ገር በእ​ው​ነ​ትም የሚ​ፈ​ርድ የለም፤ በከ​ንቱ ነገር ታም​ነ​ዋል፤ የማ​ይ​ጠ​ቅ​ማ​ቸ​ው​ንም ተና​ግ​ረ​ዋል፤ ኀጢ​አ​ትን ፀን​ሰ​ዋል፤ በደ​ል​ንም ወል​ደ​ዋል።


በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።


ገን​ዘ​ብን የሚ​ወዱ ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም ይህን ሁሉ ነገር ሰም​ተው ተጠ​ቃ​ቀ​ሱ​በት።


ሄሮ​ድ​ስም ከሠ​ራ​ዊቱ ጋር አቃ​ለ​ለው፤ አፌ​ዘ​በ​ትም፤ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብ​ስም አል​ብሶ ወደ ጲላ​ጦስ መልሶ ሰደ​ደው።


ሕዝ​ቡም ቆመው ይመ​ለ​ከቱ ነበር፤ አለ​ቆ​ችም፥ “ሌሎ​ችን አዳነ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ረጠ ክር​ስ​ቶስ ከሆነ ራሱን ያድን” እያሉ ያፌ​ዙ​በት ነበር።


ጻፎ​ችና ፈሪ​ሳ​ው​ያ​ንም የሚ​ከ​ሱ​በት ምክ​ን​ያት ያገኙ ዘንድ፥ በሰ​ን​በት ይፈ​ው​ሰው እንደ ሆነ ብለው ይጠ​ባ​በ​ቁት ነበር።


ታላቅም ድምፅ በሰማይ ሰማሁ፤ እንዲህ ሲል “አሁን የአምላካችን ማዳንና ኀይል መንግሥትም የክርስቶስም ሥልጣን ሆነ፤ ቀንና ሌሊትም በአምላካችን ፊት የሚከሳቸውየወንድሞቻችን ከሳሽ ተጥሎአልና።