እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
ዕዝራ 2:69 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደየችሎታቸውም 61,000 የወርቅ ዳሪክ፣ 5,000 ምናን ብር፣ 100 ልብሰ ተክህኖ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድሳ አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህ ምናን ብር፥ አንድ መቶ የካህናት ልብስ እንደየአቅማቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ለቤተ መቅደሱ ሥራ ማከናወኛ የሚችሉትን ያኽል አዋጥተው ያቀረቡት ስጦታ ሲደመር አምስት መቶ ኪሎ ወርቅ፥ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ስድስት ኪሎ ብር ሆነ፤ ለካህናቱም የሚሆን አንድ መቶ የካህናት ልብስ ሰጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድሳ አንድ ሺህም የወርቅ ዳሪክ፥ አምስት ሺህም ምናን ብር፥ አንድ መቶም የካህናት ልብስ እንደ ችሎታቸው ወደ ሥራው ቤተ መዛግብት አቀረቡ። |
እንዲሁም ንጉሡ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት የአሠራው ሥራ ሁሉ ተፈጸመ። አባቱም ዳዊት የቀደሰውን፥ ራሱም የቀደሰውን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ በነበሩ ግምጃ ቤቶች አገባ።
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።
ለእግዚአብሔርም ቤት ሥራ አምስት ሺህ መክሊት ወርቅና ዐሥር ሺህ ዳሪክ፥ ዐሥር ሺህም መክሊት ብር፥ ዐሥራ ስምንት ሺህም መክሊት ናስ፥ መቶ ሺህም መክሊት ብረት ሰጡ።
በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ ጊዜ ከአባቶች ቤቶች አለቆች አያሌዎች ለእግዚአብሔር ቤት በስፍራው ይሠሩት ዘንድ በፈቃዳቸው ሰጡ።