La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር በበ​ላዩ ከነ​በ​ረ​በት ኪሩብ ተነ​ሥቶ ወደ ቤቱ መድ​ረክ ሄዶ ነበር፤ በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን፥ የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂ​ያም በወ​ገቡ የታ​ጠ​ቀ​ውን ሰው ጠራ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ የእስራኤል አምላክ ክብር ከነበረበት ከኪሩብ በላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መድረክ ሄደ። እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውን በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበውን ሰው ጠራ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤልም አምላክ ክብር በላዩ ላይ አርፎ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መግቢያ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን በወገቡም የጸሐፊ ቀለም ቀንድ የያዘውን ሰው ጠራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የእስራኤልን አምላክ ክብር የሚገልጥ ነጸብራቅ ቀድሞ ካረፈበት ከኪሩብ ላይ ተነሥቶ ወደ ቤተ መቅደሱ መግቢያ በር ሄደ፤ እግዚአብሔርም በፍታ የለበሰውንና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር የያዘውን ሰው፥ ጠራው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤልም አምላክ ክብር በበላዩ ከነበረበት ኪሩብ ተነሥቶ ወደ ቤቱ መድረክ ሄዶ ነበር፥ በፍታ የለበሰውን የጸሐፊውንም ቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘውን ሰው ጠራ።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 9:3
6 Referencias Cruzadas  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብ​ርም ከኪ​ሩ​ቤል ወጥቶ በቤቱ መድ​ረክ ላይ ቆመ፤ ቤቱም በደ​መ​ናው ተሞላ፤ አደ​ባ​ባ​ዩም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ፀዳል ተሞላ።


እኔም ተነ​ሥቼ ወደ ሜዳው ሄድሁ፤ እነ​ሆም በኮ​ቦር ወንዝ እን​ዳ​የ​ሁት ክብር ያለ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በዚያ ቆሞ ነበር፤ በግ​ም​ባ​ሬም ተደ​ፋሁ።


እነ​ሆም ቀድሞ በሜዳ እንደ አየ​ሁት ራእይ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር በዚያ ነበረ።


እነ​ሆም እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው ገጀሞ መሣ​ሪያ በእ​ጃ​ቸው ይዘው ስድ​ስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚ​መ​ለ​ከ​ተው ከላ​ይ​ኛው በር መን​ገድ መጡ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የበ​ፍታ ልብስ የለ​በ​ሰና የሰ​ን​ፔር መታ​ጠ​ቂያ በወ​ገቡ የታ​ጠቀ አንድ ሰው ነበረ። እነ​ር​ሱም ገብ​ተው በናሱ መሠ​ዊያ አጠ​ገብ ቆሙ።