ሰውንና ወንድሙን፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ እበትናቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራላቸውም፤ አላዝንላቸውም፤ አልምራቸውምም።”
ሕዝቅኤል 7:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይኔም አይራራልሽም፤ እኔም ይቅር አልልሽም፤ መንገድሽንም አመጣብሻለሁ፤ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ነው፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርኅራኄ ዐይን አልመለከትሽም፤ ምሕረትም አላደርግልሽም፤ ስለ አካሄድሽና በመካከልሽ ስላለው ጸያፍ ተግባር፣ ተገቢውን ቅጣት እከፍልሻለሁ፤ በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይኔ አይራራልሽም እኔም አላዝንም፤ መንገድሽን በአንቺ ላይ እመልስብሻለሁ፥ ርኩሰቶችሽም በመካከልሽ ይሆናሉ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከቶ አልራራላችሁም፤ ምሕረትም አላደርግላችሁም። በርኲሰት ላይ እስካላችሁ ድረስ እንደ አካሄዳችሁ እቀጣችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይኔም አይራራልሽም እኔም አላዝንም፥ መንገድሽንም አመጣብሻለሁ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ይሆናል፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። |
ሰውንና ወንድሙን፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ እበትናቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አጠፋቸዋለሁ እንጂ አልራራላቸውም፤ አላዝንላቸውም፤ አልምራቸውምም።”
ምድሬንም በተጠሉ በጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኀጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”
ብዙ አሕዛብና ታላላቆች ነገሥታት እነርሱን ይገዙአቸዋል፤ እኔም እንደ አደራረጋቸውና እንደ እጃቸው ሥራ እከፍላቸዋለሁ።”
ጣዖት በሚያመልኩበት ልባቸውና በኀጢአታቸው እንደ ልባቸው ቢሄዱ መንገዳቸውን በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ይጠፋሉ፤ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
የሕፃንነትሽን ወራት አላሰብሽምና፥ በዚህም ነገር ሁሉ አስቈጥተሽኛልና፤ ስለዚህ እነሆ እኔ ደግሞ መንገድሽን በራስሽ ላይ አመጣለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ እንደዚህም በበደልሽ ሁሉ ላይ ኀጢአትን ሠራሽ።
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”
እንግዲህ በደላችሁ በላያችሁ ላይ ይመለሳል፤ እናንተም የጣዖቶቻችሁን ኀጢአት ትሸከማላችሁ፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።”
እኔ እግዚአብሔር ተናግሬአለሁ፤ እመጣለሁ፤ እኔም አደርገዋለሁ፤ አልተውም፤ አልራራም፤ አልጸጸትም፤ እንደ መንገድሽና እንደ ሥራሽም እፈርድብሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። ስለዚህ የሰውን ደም እንደ አፈሰስሽ እኔ እፈርድብሻለሁ፤ እንደ ኀጢአትሽም ተበቅዬ አጠፋሻለሁ፤ ስምሽም ጐሰቈለ፥ ብዙ ኀዘንንም ታዝኛለሽ።”
ስለዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእድፍሽና በርኵሰትሽ መቅደሴን ስላረከስሽ፥ ስለዚህ በእውነት እኔ አሳንስሻለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም።
እጄንም እዘረጋባቸዋለሁ፤ በሚኖሩበትም ስፍራ ሁሉ ምድሪቱን ከዴብላታ ምድረ በዳ ይልቅ ውድማና በረሃ አደርጋታለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
ንጉሡም ያለቅሳል፥ አለቃም ውርደትን ይለብሳል፤ የምድርም ሕዝብ እጅ ትሰላለች፤ እንደ መንገዳቸውም መጠን አደርግባቸዋለሁ፤ በፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።”
አሁንም ፍጻሜ በአንቺ ላይ ደርሶአል። ቍጣዬንም እሰድድብሻለሁ፤ እንደ መንገድሽም መጠን እፈርድብሻለሁ፤ ጕስቍልናሽንም ሁሉ አመጣብሻለሁ።
ዐይኔም አይራራም፤ እኔም ይቅር አልልም፤ መንገድሽንም አመጣብሻለሁ፤ ርኵሰትሽም በመካከልሽ ነው፤ እኔም እግዚአብሔር የምቀሥፍ እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
ስለዚህ እኔ ደግሞ በመዓት እሠራለሁ፤ ዐይኔ አይራራም፤ እኔም ይቅርታ አላደርግም፤ ወደ ጆሮዬም በታላቅ ድምፅ ቢጮኹ አልሰማቸውም” አለኝ።
ኤፍሬም ግን ክብርንና ከንቱ ነገርን የሚያሳድድ ክፉ ጋኔን ነው። ሁልጊዜም ሐሰትንና ተንኰልን ያበዛል፤ ከአሦርም ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋል፤ ምሕረትም ያደርጉለት ዘንድ ወደ ግብፅ ዘይትን ይልካል።
የበቀል ወራት መጥቶአል፤ የፍዳም ወራት ደርሶአል፤ እስራኤልም እንደ አበደ ነቢይና ርኩስ መንፈስ እንደ አለበት ሰው ይታመማል፤ ከኀጢአትህና ከጠላትነትህ ብዛት የተነሣም ቍጣህን አበዛህ።
እግዚአብሔርም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “ቱንቢ ነው” አልሁ። ጌታም፥ “እነሆ! በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱንቢ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም።
ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም።
“እኔ እበቀላለሁ፤ እኔም ብድራትን እመልሳለሁ፥” ያለውን እናውቀዋለንና፤ ዳግመኛም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል።”