La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ማቅም ትታ​ጠ​ቃ​ላ​ችሁ፤ ድን​ጋ​ጤም ይሸ​ፍ​ና​ች​ኋል፤ በፊ​ትም ሁሉ ላይ ሐፍ​ረት ይሆ​ናል፤ በራ​ሳ​ች​ሁም ሁሉ ላይ ቡሃ​ነት ይሆ​ናል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ማቅ ይለብሳሉ፤ ሽብርም ይውጣቸዋል። ፊታቸው ኀፍረት ይለብሳል፤ ራሳቸውም ይላጫል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ማቅ ይለብሳሉ፥ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በሁሉም ፊቶች ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውም ሁሉ መላጣ ይሆናል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ማቅ ይለብሳሉ፤ ድንጋጤ ይይዛቸዋል፤ በፊቶቻቸው ላይ ኀፍረት ይታያል፤ ራሳቸውንም ይላጫሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ማቅም ይለብሳሉ ድንጋጤም ይሸፍናቸዋል፥ በፊትም ሁሉ ላይ እፍረት ይሆናል፥ ራሳቸውንም ሁሉ ይነጩታል።

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 7:18
14 Referencias Cruzadas  

ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ በአ​ብ​ራም ድን​ጋጤ መጣ​በት፤ እነ​ሆም፥ የሚ​ያ​ስ​ፈራ ጽኑዕ ጨለማ መጣ​በት፤


እኔ ባሰ​ብሁ ቍጥር እጨ​ነ​ቃ​ለሁ፤ ጻዕ​ርም ሥጋ​ዬን ይይ​ዛል።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁ​ን​ብሽ፤ በወ​ርቅ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸ​ላ​ሽም ፋንታ ቡሃ​ነት ይው​ጣ​ብሽ፤ በሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።


ከት​ን​ሽ​ነ​ታ​ችን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኛና አባ​ቶ​ቻ​ችን በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኀጢ​አት ሠር​ተ​ና​ልና፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ን​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል አል​ሰ​ማ​ን​ምና በእ​ፍ​ረ​ታ​ችን ተኝ​ተ​ናል፤ ውር​ደ​ታ​ች​ንም ሸፍ​ኖ​ናል።”


በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃ​ነት አለ፤ ጽሕ​ማ​ቸ​ውን ሁሉ ይላ​ጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ሁሉም በወ​ገ​ባ​ቸው ማቅን ይታ​ጠ​ቃሉ።


የጠ​ላት ሰይፍ ከብ​በ​ዋ​ች​ኋ​ልና ወደ ሜዳ አት​ውጡ፤ በመ​ን​ገ​ድም ላይ አት​ሂዱ።


የሕ​ዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራ​ስ​ሺም ላይ አመድ ነስ​ንሺ፥ አጥፊ በላ​ያ​ችን በድ​ን​ገት ይመ​ጣ​ብ​ና​ልና ለተ​ወ​ዳጅ ልጅ እን​ደ​ሚ​ደ​ረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አል​ቅሺ።


ስለ አን​ቺም የራ​ሳ​ቸ​ውን ጠጕር ይላ​ጫሉ፤ ማቅም ያሸ​ር​ጣሉ፤ በነ​ፍ​ስም ምሬት ስለ አንቺ መራራ ልቅ​ሶን ያለ​ቅ​ሳሉ።


መሥ​ዋ​ዕ​ቱና የመ​ጠጡ ቍር​ባን ከአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ቤት ቀር​ቶ​አ​ልና እና​ንተ ካህ​ናት! ማቅ ታጥ​ቃ​ችሁ አል​ቅሱ፤ እና​ን​ተም የመ​ሠ​ውያ አገ​ል​ጋ​ዮች! ዋይ በሉ፤ እና​ን​ተም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋ​ዮች ኑና በማቅ ላይ ተኙ።


ዓመት በዓ​ላ​ች​ሁ​ንም ወደ ልቅሶ፥ ዝማ​ሬ​ያ​ች​ሁ​ንም ወደ ዋይታ እለ​ው​ጣ​ለሁ፤ ማቅ​ንም በወ​ገብ ሁሉ ላይ፥ ቡሃ​ነ​ት​ንም በራስ ሁሉ ላይ ላይ አመ​ጣ​ለሁ፤ እንደ ወዳጅ ልቅሶ አደ​ር​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት እንደ መከራ ቀን ይሆ​ናሉ።