La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሕዝቅኤል 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ላሉት አሕ​ዛብ ሰበብ ሆና​ች​ኋ​ልና፥ በት​እ​ዛ​ዜም አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​ምና፥ ፍር​ዴ​ንም አል​ጠ​በ​ቃ​ች​ሁ​ምና፥ በዙ​ሪ​ያ​ች​ሁም እንደ አሉ እንደ አሕ​ዛብ ፍርድ እንኳ አላ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ምና፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብ ይልቅ ሞገደኞች ሆናችኋል፤ ሥርዐቴን አልተከተላችሁም፤ ለሕጌም አልታዘዛችሁም። በዙሪያችሁ የሚገኙ አሕዛብ የሚጠብቁትን ሕግ እንኳ አልጠበቃችሁም።’

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሁካታችሁ በዙሪያችሁ ካሉት አገሮች ይልቅ ሆኗል፥ በትእዛዜም አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አልጠበቃችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንዳሉ እንደ አሕዛብ ፍርድ እንኳ አላደረጋችሁምና

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር የሚለው እንዲህ ነው፦ “እናንተ የኢየሩሳሌም ኗሪዎች! በዙሪያችሁ ካሉት ሕዝቦች ይበልጥ ሥርዓተ አልበኞች ሆናችኋል፤ ሕጎቼንና ሥርዓቴን አላከበራችሁም፤ በአካባቢአችሁ ባሉት ሕዝቦች ሥርዓት እንኳ አልተመራችሁም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዙሪያችሁ ላሉት አሕዛብ ሰበብ ሆናችኋልና፥ በትእዛዜም አልሄዳችሁምና፥ ፍርዴንም አልጠበቃችሁምና፥ በዙሪያችሁም እንዳሉ እንደ አሕዛብ ፍርድ እንኳ አላደረጋችሁምና

Ver Capítulo



ሕዝቅኤል 5:7
6 Referencias Cruzadas  

ምና​ሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ካጠ​ፋ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ ይልቅ ክፉ ይሠሩ ዘንድ በይ​ሁ​ዳና በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን አሳተ።


ፍዳ​ሽ​ንም ትቀ​በዪ ዘንድ በአ​ስ​ቈ​ጣ​ሽኝ ሥራሽ ሁሉ ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


ስለ​ዚህ እኔ ሕያው ነኝና በእ​ድ​ፍ​ሽና በር​ኵ​ሰ​ትሽ መቅ​ደ​ሴን ስላ​ረ​ከ​ስሽ፥ ስለ​ዚህ በእ​ው​ነት እኔ አሳ​ን​ስ​ሻ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ዐይ​ኔም አይ​ራ​ራም፤ እኔም ይቅር አል​ልም።