ሕዝቅኤል 48:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግዚአብሔር የምትለዩት መባ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ወርዱም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የዚህ መባ ርዝመት ሃያ ዐምስት ሺሕ ክንድ ሲሆን፣ ስፋቱ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለጌታ የምታቀርቡት መባ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱ ደግሞ አስር ሺህ ክንድ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ክልል መካከል ርዝመቱ ኻያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ሺህ ክንድ የሆነ ቦታ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት መባ ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል። |
“ርስትም አድርጋችሁ ምድርን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድር የተቀደሰውን የዕጣ ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ እግዚአብሔር ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ሁሉ ዙሪያው የተቀደሰ ይሆናል።
የመቅደሱም ቀዳምያት ለካህናቱ ይሆናል፤ በሰሜን በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ፥ በምዕራብም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በምሥራቅም በኩል ወርዱ ዐሥር ሺህ፥ በደቡብም በኩል ርዝመቱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል። የእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ በመካከሉ ይሆናል።
“ከይሁዳም ድንበር ቀጥሎ ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ለመባ የተለየ ክፍል ይሆናል፤ ወርዱ ሃያ አምስት ሺህ ክንድ ይሆናል፤ ርዝመቱም ከምሥራቅ ጀምሮ እስከ ምዕራብ ድረስ ከዕጣ ክፍሎች እንደ አንዱ ይሆናል፤ ቤተ መቅደሱም በመካከሉ ይሆናል።
በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ፥ “እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውን ከተሞች፥ ለከብቶቻችንም መሰማሪያዎች ትሰጡን ዘንድ አዝዞአል” ብለው ተናገሩአቸው።