ሕዝቅኤል 41:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነበሩት አረፍቶች ምክንያት ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር፤ ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው፥ ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ሦስተኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያሉት ክፍሎች ስፋት በየደርቡ እየጨመረ የሚሄድ ነው። በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ያለው ሕንጻ አሠራሩ ከታች ወደ ላይ እየሰፋ የሚሄድ በመሆኑ፣ ወደ ላይ በተሄደ ቍጥር የክፍሎቹ ስፋት እየጨመረ የሚሄድ ነው። በመካከለኛው ደርብ በኩል አድርጎ ከታች ወደ ላይ የተዘረጋም ደረጃ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነበሩት አረፍቶች ምክንያት ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር፤ ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታችኛው ግድግዳ ከፎቁ ግድግዳ የወፈረ ነው፤ ሆኖም ከውጪ ሲመለከቱት ከላይ እስከ ታች ያለው ግድግዳ እኩል ውፍረት ያለው ይመስላል። ግድግዳዎቹ ከታች ወደላይ እየሳሱ ስለሚሄዱ ወደ ላይ በተወጣ ቊጥር ክፍሎቹ እየሰፉ ይሄዳሉ። መወጣጫዎቹም ከምድር ወደ ላይኛው ፎቅ የሚወጡት በመካከለኛው ፎቅ በኩል አድርገው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቤቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነበሩት አረፍቶች ምክንያት ላይኞቹ ጓዳዎች ከታችኞቹ ጓዳዎች ይበልጡ ነበር፥ ከታችኛውም ደርብ ወደ መካከለኛው ከመካከለኛውም ደርብ ወደ ላይኛው የሚወጣበት ደረጃ ነበረ። |
የታችኛውም ደርብ ጓዳዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠገብ ነበረ። ከዚያም ወደ መካከለኛው ደርብ፥ ከመካከለኛውም ወደ ሦስተኛው ደርብ የሚወጡበት መውጫ ነበረው።
እርስዋም ከዘር ሁሉ ታንሳለች፤ በአደገች ጊዜ ግን፥ ከአታክልቶች ትበልጣለች የሰማይም ወፎች መጥተው በቅርንጫፎችዋ እስኪሰፍሩ ድረስ ዛፍ ትሆናለች።”
ስለዚህም የክርስቶስን የነገሩን መጀመሪያ ትተን ወደ ፍጻሜው እንሂድ፤ እንግዲህ ደግሞ ሌላ መሠረት እንዳትሹ ዕወቁ፤ ይኸውም ከሞት ሥራ ለመመለስ፥ በእግዚአብሔርም ለማመን፥