ሕዝቅኤል 41:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመግቢያውም ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ፥ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝመቱንም አርባ ክንድ፥ ወርዱንም ሃያ ክንድ አድርጎ ለካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመግቢያውም በር ወርድ ዐሥር ክንድ ሲሆን፣ በግራና በቀኝ በኩል ወጣ ወጣ ያሉት ግንቦች ወርድ ዐምስት ክንድ ነበር። ደግሞም የውስጡን መቅደስ ለካ፤ ርዝመቱ አርባ ክንድ፣ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመግቢያው ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያው መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያ ወገን ደግሞ አምስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝመቱን አርባ ክንድ ወርዱን ደግሞ ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወርዱም ዐሥር ክንድ ሆነ፤ በግራና ቀኝ የሚገኙትም ግንቦች የእያንዳንዱ ውፍረት አምስት ክንድ ነበር፤ የተቀደሰው ስፍራ ሲለካ ርዝመቱ አርባ ክንድ፥ ወርዱም ኻያ ክንድ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመግቢያውም ወርድ አሥር ክንድ ነበረ፥ የመግቢያውም መቃኖች በዚህ ወገን አምስት ክንድ በዚያም ወገን አምስት ክንድ ነበሩ፥ ርዝመቱንም አርባ ክንድ ወርዱንም ሀያ ክንድ አድርጎ ለካ። |
ደግሞም የእግዚአብሔርን ቤት ደጆች ዘግተዋል፤ መብራቶቹንም አጥፍተዋል፤ በመቅደሱም ውስጥ ለእስራኤል አምላክ አላጠኑም፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አላቀረቡም።
ሰሎሞንም የእግዚአብሔርን ቤት ይሠራ ዘንድ የጣለው መሠረት ይህ ነው፤ ርዝመቱም በዱሮው ስፍር ስድሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ ክንድ ነበረ።
ቤቱንም፥ ሰረገሎቹንም፥ መድረኮቹንም፥ ግንቦቹንም፥ ደጆቹንም በወርቅ ለበጠ፤ በግንቦቹም ላይ ኪሩቤልን ቀረጸ።
ለድንኳኑ ደጃፍም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይ ግምጃም ከተፈተለ ከጥሩ በፍምታም በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አድርግለት።
ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አሠራር የተሠራ መጋረጃ አደረጉ፤
ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።