የምሥራቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦስቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።
ሕዝቅኤል 40:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበሩንም ደጀ ሰላም ስምንት ክንድ፤ የግንቡንም አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ፤ የበሩም ደጀ ሰላም በስተውስጥ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቁመቱ ስምንት ክንድ፣ የዐምዶቹም ውፍረት ሁለት ክንድ ነበር። የመግቢያው በር መተላለፊያ በረንዳ፣ ከቤተ መቅደሱ ትይዩ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበሩን መተላለፊያ ስምንት ክንድ፥ የግንቡንም አዕማድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ፤ የበሩም መተላለፊያ በውስጥ በኩል ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበሩንም ደጀ ሰላም ስምንት ክንድ፥ የግንቡንም አዕማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድርጎ ለካ፥ የበሩም ደጀ ሰላም በስተ ውስጥ ነበረ። |
የምሥራቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦስቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።
በደጀ ሰላሙም በሁለቱ ወገን በዚህና በዚያ የዐይነ ርግብ መስኮቶችና የተቀረጹ የዘንባባ ዛፎች ነበሩበት፤ የመቅደሱም ጓዳዎችና የእንጨቱ መድረክ እንዲሁ ነበሩ።
አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ ይቀመጥባታል፤ በበሩ ይገባል፤ በዚያም መንገድ ይወጣል።”
ካህኑም ከኀጢአቱ መሥዋዕት ደም ወስዶ በመቅደሱ መቃኖችና በመሠዊያው እርከን በአራቱ ማዕዘን፥ በውስጠኛውም አደባባይ በበሩ መቃኖች ላይ ይርጨው።