የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
ሕዝቅኤል 40:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝመት አንድ ዘንግ፤ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶቹም መካከል አምስት ክንድ ነበረ፤ በበሩም ደጀ ሰላም፤ በስተውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ የመድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዘብ ጠባቂ ቤቶች፣ ቁመታቸው አንድ መለኪያ ዘንግ፣ ወርዳቸውም አንድ መለኪያ ዘንግ ነበር፤ በቤቶቹም መካከል ያሉት ግንቦች ውፍረት ዐምስት ክንድ ነበር። ከቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት ባለው መተላለፊያ በረንዳ አጠገብ በውስጥ በኩል ያለው የበሩ መድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፍሉም ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነበረ፤ ከበራፉም በውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ መተላለፊያ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ዘንግ ቁመትና አንድ ዘንግ ወርድ ያላቸው የዘብ ማረፊያ ክፍሎች ነበሩት፤ በማረፊያ ክፍሎቹ መካከል ያለው ርቀት አምስት ክንድ ነው፤ የቅጽሩ በር መግቢያ መድረክ ወደ ውስጥ እስከሚያስገባው መተላለፊያ ጫፍ ድረስ አንድ ዘንግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዘበኛውም ጓዳ ሁሉ ርዝመቱ አንድ ዘንግ፥ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ፥ በዘበኛውም ጓዳዎች መካከል አምስት ክንድ ነበረ፥ በበሩም ደጀ ሰላም በስተ ውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ የመድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ። |
የእግዚአብሔርንም ቤት በየአደባባዩና በየመጋረጃው ውስጥ ለማገልገል፥ ቅዱሱንም ዕቃ ሁሉ ለማንጻት፥ የእግዚአብሔርንም ቤት አገልግሎት ለመሥራት ከአሮን ልጆች እጅ በታች ሹሞአቸው ነበር።
እነዚህ አራቱ ኀያላን ሰዎች ለአራቱ በሮች ኀላፊዎች ነበሩ። ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ የተሾሙ ነበሩ።
በካህናትና በሌዋውያን አለቆች፥ በእስራኤልም አባቶች ቤቶች አለቆች ፊት በኢየሩሳሌም በእግዚአብሔር ቤት ጓዳዎች ውስጥ እስክትመዝኑ ድረስ ተግታችሁ ጠብቁ” አልኋቸው።
ወደ እግዚአብሔርም ቤት በበረኛው በሰሎም ልጅ በማሴው ጓዳ በላይ ባለው በአለቆቹ ጓዳ አጠገብ ወደ አለው ወደ እግዚአብሔር ሰው ወደ ጎዶልያ ልጅ ወደ ሐናንያ ልጆች ጓዳ አገባኋቸው።
የምሥራቁም ዕቃ ቤቶች በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚያም በኩል ሦስት፥ ነበሩ፤ ለሦስቱም አንድ ልክ ነበረ፤ የግንቡም አዕማድ ወርድ በዚህ በኩልና በዚያ በኩል አንድ ልክ ነበረ።
የዕቃ ቤቶቹም በዚህ በኩል ሦስት፥ በዚያም በኩል ሦስት ነበሩ፤ የግንቡ አዕማድና መዛነቢያዎቹም፥ ወደ ምሥራቅ የሚያሳዩ ዘንባባዎቹም አምሳ ክንድ ነበሩ፤ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
እንደዚያውም መጠን አድርጎ የዕቃ ቤቶቹንና የግንቡን አዕማድ፥ መዛነቢያዎቻቸውንም ለካ፤ በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱ አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
እንደዚያም መጠን የዕቃ ቤቶቹንና የግንቡን አዕማድ፥ መዛነቢያዎቹንም ለካ፤ በእርሱና በመዛነቢያዎቹም ዙሪያ መስኮቶች ነበሩ፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።
የዕቃ ቤቶቹንና የግንቡን አዕማድ፥ መዛነቢያዎቹንም ለካ፤ በዙሪያውም መስኮቶች ነበሩበት፤ ርዝመቱም አምሳ ክንድ፥ ወርዱም ሃያ አምስት ክንድ ነበረ።