የታችኛውም ደርብ ጓዳዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠገብ ነበረ። ከዚያም ወደ መካከለኛው ደርብ፥ ከመካከለኛውም ወደ ሦስተኛው ደርብ የሚወጡበት መውጫ ነበረው።
ሕዝቅኤል 40:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር መጣ፤ በሰባቱም ደረጃዎች ላይ ወጣ፤ በበሩ በኩል ያለውንም የመድረኩን ወለል ወርዱን አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ፤ የሁለተኛውም ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በምሥራቅ ትይዩ ወዳለው በር መጣ፤ ደረጃዎቹን ወጥቶ የበሩን መግቢያ መድረክ ለካ፤ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊቱ ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በር መጣ፥ በደረጃዎቹም ወጥቶ በበሩ በኩል ያለውን የቤቱን መግቢያ ወለል ወርዱን ለካ አንድ ዘንግ ነበር፥ የሌላኛውም የቤቱ መግቢያ ወለል ወርድ አንድ ዘንግ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ በስተምሥራቅ በኩል ወዳለው የቅጽር በር አልፎ ሄደ፤ ደረጃውንም ወጥቶ ከጫፉ የመድረኩን ወለል ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተውም በር መጣ በደረጃዎቹም ላይ ወጣ፥ በበሩ በኩል ያለውንም የመድረኩን ወለል ወርዱን አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ። |
የታችኛውም ደርብ ጓዳዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠገብ ነበረ። ከዚያም ወደ መካከለኛው ደርብ፥ ከመካከለኛውም ወደ ሦስተኛው ደርብ የሚወጡበት መውጫ ነበረው።
ከዚያም በኋላ የሄሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አንጻር ያለውን ሠራ። ከእርሱም በኋላ የምሥራቁ በር ጠባቂ የሴኬንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።
መንፈስም አነሣኝ፤ ወደ ምሥራቅም አንጻር ወደሚያሳየው ወደ እግዚአብሔር ቤት በር ወሰደኝ። እነሆም በበሩ መግቢያ ሃያ አምስት ሰዎች ነበሩ፤ በመካከላቸውም የሕዝቡን አለቆች የዓዙርን ልጅ ያእዛንያንና የበናያስ ልጅ ፈላጥያን አየሁ።
መስኮቶቹም፥ መዛነቢያዎቹም፥ የዘንባባ ዛፎቹም ወደ ምሥራቅ እንደሚመለከተው በር ልክ ነበሩ፤ ወደ እርሱም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ መዛነቢያዎቹም በፊቱ ነበሩ።
ወደ ደቡብም መራኝ፤ እነሆም ወደ ደቡብ የሚመለከት በር ነበረ፤ የግንቡን አዕማድና መዛነቢያዎቹንም እንደዚያው መጠን አድርጎ ለካ።
ወደ እርሱም የሚያደርሱ ሰባት ደረጃዎች ነበሩ፤ መዛነቢያዎቹም በፊቱ ነበሩ፤ በግንቡም አዕማድ ላይ አንዱ በዚህ አንዱም በዚያ ወገን ሆኖ የዘንባባ ዛፍ ተቀርጾባቸው ነበር።
እነሆም በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፤ በሰውየውም እጅ የክንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድስት ክንድ ያለበት የመለኪያ ዘንግ ነበረ፤ የቅጥሩንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ።
የዕቃ ቤቱ ሁሉ ርዝመት አንድ ዘንግ፤ ወርዱም አንድ ዘንግ ነበረ፤ በዕቃ ቤቶቹም መካከል አምስት ክንድ ነበረ፤ በበሩም ደጀ ሰላም፤ በስተውስጥ በኩል የሚገኝ የበሩ የመድረክ ወለል አንድ ዘንግ ነበረ።
መድረኮቹ፥ መስኮቶቹና አዕማዱ፥ በስተውስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላሙም በእንጨት ተለብጠው ነበር፤ በሦስቱም ዙሪያ የዐይነ ርግብ መስኮቶች ነበሩ። መቅደሱም በመድረኩ አንጻር ከመሬት ጀምሮ እስከ መስኮቶቹ ድረስ በእንጨት ተለብጦ ነበር፤ መስኮቶቹም የዐይነ ርግብ ነበሩ፤
የእርከኑም ርዝመት ዐሥራ አራት ክንድ፥ ወርዱም ዐሥራ አራት ክንድ ነው፤ አራቱም መዐዝን ትክክል ነው፤ በዙሪያውም ያለው ክፈፍ የክንድ እኩሌታ ነው፤ መሠረቱም በዙሪያው አንድ ክንድ ነው፤ ደረጃዎቹም ወደ ምሥራቅ ይመለከታሉ።”
መድረካቸውን በመድረኬ አጠገብ፥ መቃናቸውንም በመቃኔ አጠገብ አድርገዋልና። በእኔና በእነርሱ መካከል ግንብ ብቻ ነበረ፤ በሠሩትም ርኵሰት ቅዱስ ስሜን አረከሱ፤ ስለዚህ በቍጣዬ አጠፋኋቸው።
አለቃውም በፈቃዱ የሚያቀርበውን መሥዋዕት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት፥ ወይም በፈቃዱ ለእግዚአብሔር የሚያቀርበውን የደኅንነቱን መሥዋዕት በአቀረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥራቅ የሚመለከተው በር ይከፈትለት፤ በሰንበትም ቀን እንደሚያደርግ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ያቅርብ፤ ከዚያም በኋላ ይውጣ፤ ከወጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።
ወደ መቅደሱም መዝጊያ መለሰኝ፤ እነሆም ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፤ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ ከቀኝ ወገን በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ፥ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።