በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፥ አንደበታችንም ሐሤትን አደረገ፤ በዚያን ጊዜ አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው” አሉ።
ሕዝቅኤል 40:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፤ በሰውየውም እጅ የክንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድስት ክንድ ያለበት የመለኪያ ዘንግ ነበረ፤ የቅጥሩንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤተ መቅደሱን ዙሪያ ሙሉ በሙሉ የከበበ ቅጥር አየሁ፤ በሰውየውም እጅ ርዝመቱ ስድስት ክንድ የሆነ መለኪያ ዘንግ አየሁ፤ እያንዳንዱ ክንድ፣ አንድ ክንድ ከስንዝር ነበር፤ እርሱም ቅጥሩን ለካው፤ ስፋቱ አንድ መለኪያ ዘንግ ሲሆን፣ ቁመቱም እንዲሁ አንድ መለኪያ ዘንግ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ ያለው የመለኪያው ዘንግ ርዝመት አንድ ክንድ ከስንዝር የሆነ ስድስት ክንድ ነበረ፤ ቅጥሩንም ለካ፥ ስፋቱ አንድ ዘንግ፥ ቁመቱም አንድ ዘንግ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱ ዙሪያ ቅጥር ነበረ፤ በሰውዬው እጅ ያለው መለኪያ ዘንግ በእርሱ ረጃጅም ክንዶች ስድስት ይሆናል፤ የቅጽሩ ስፋት ሲለካ አንድ ዘንግ፥ ከፍታው ሲለካ አንድ ዘንግ ሆነ። የእርሱ ክንድ ግን በሌሎች ሰዎች ክንድ ሲለካ አንድ ክንድ ከጋት ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ በቤቱ ውጭ በዙሪያው ቅጥር ነበረ፥ በሰውዬውም እጅ የክንዱ ልክ አንድ ክንድ ከጋት የሆነ ስድስት ክንድ ያለበት የመለኪያ ዘንግ ነበረ፥ የቅጥሩንም ስፋት አንድ ዘንግ ቁመቱንም አንድ ዘንግ አድርጎ ለካ። |
በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን ሞላ፥ አንደበታችንም ሐሤትን አደረገ፤ በዚያን ጊዜ አሕዛብ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው” አሉ።
በዚያም ቀን ይህን ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘምራሉ፤ እነሆም፥ የጸናችና የምታድን፥ ቅጥርንና ምሽግንም የምታደርግ ከተማ አለችን።
እንግዲህ በምድርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳርቻሽም ውስጥ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ አይሰማም፤ ቅጥሮችሽ ድኅነት ይባላሉ፤ በሮችሽም በጥርብ ድንጋይ ይሠራሉ።
ለመቅደሱም ከፍ ያለ ወለል በዙሪያው እንዳለው አየሁ፤ የጓዳዎቹም መሠረት ቁመቱ ሙሉ ዘንግ የሚያህል ስድስት ክንድ ነበረ።
በአራቱም ወገን ለካ፤ የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ፥ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።
የመሠዊያው ልክ በክንድ ይህ ነው፤ ክንዱም ክንድ ተጋት ነው። የመሠረቱም ቁመቱ አንድ ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ ነው፤ አንድ ስንዝርም ክፈፍ ዳር ዳሩን በዙሪያው አለ፤ የመሠዊያው ቁመት እንዲሁ ነው።
ከራፋይንም ወገን የባሳን ንጉሥ ዐግ ብቻውን ቀርቶ ነበር፤ እነሆ፥ አልጋው የብረት አልጋ ነበረ፤ እርሱ በአሞን ልጆች ሀገር ዳርቻ አለ፤ ርዝመቱ ዘጠኝ ክንድ ወርዱም አራት ክንድ በሰው ክንድ ልክ ነበረ።
ታላቅና ረጅም ቅጥር ነበራት፤ ዐሥራ ሁለትም ደጆች ነበሩአት፤ በደጆቹም ዐሥራ ሁለት መላእክት ቆሙ የዐሥራ ሁለቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተጽፈውባቸው ነበር።