ፍርዴን ለተስፋ ይቅርታዬንም ለትክክለኛ ሚዛን አደርጋለሁ፤ በከንቱና በሐሰት የሚታመኑ ከዐውሎ ነፋስ አያመልጡም።
ሕዝቅኤል 40:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደዚያም አመጣኝ፤ እነሆም መልኩ እንደሚያንፀባርቅ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደዚያ ወሰደኝ፤ እነሆ መልኩ ናስ የሚመስል ሰው አየሁ፤ እርሱም የሐር ገመድና መለኪያ ዘንግ በእጁ ይዞ በመግቢያው በር ላይ ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆ፥ መልኩ ናስ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ይዞ ነበረ፤ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደዚያ ሲወስደኝም እንደ ነሐስ የሚያበራ መልክ ያለውን አንድ ሰው አየሁ፤ እርሱም ከበፍታ የተሠራ ገመድና መለኪያ ዘንግ ይዞ በቅጽሩ በር አጠገብ ቆሞ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደዚያም አመጣኝ፥ እነሆም፥ መልኩ እንደ ናስ መልክ የመሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፥ በእጁም የተልባ እግር ገመድና የመለኪያ ዘንግ ነበረ፥ እርሱም በበሩ አጠገብ ቆሞ ነበር። |
ፍርዴን ለተስፋ ይቅርታዬንም ለትክክለኛ ሚዛን አደርጋለሁ፤ በከንቱና በሐሰት የሚታመኑ ከዐውሎ ነፋስ አያመልጡም።
ከወገቡም አምሳያ ወደ ላይ የሚብለጨለጭ የወርቅ አምሳያ አየሁ፤ ከወገቡም አምሳያ ወደ ታች እንደ እሳት አምሳያ አየሁ፤ በዙሪያውም ፀዳል ነበረ።
እግሮቻቸውም ቀጥ ያሉ ነበሩ፤ የእግራቸው ሰኰና እንደ ላም እግር ሰኰና ነበረ፤ እንደ ተወለወለ ናስም ይብለጨለጭ ነበር።
ሰውዮውም የመለኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፤ ውኃውም እስከ ቍርጭምጭሚት ደረሰ።
እኔም አየሁ፤ እነሆም ከወገቡ በታች እንደ እሳት የሚመስል የሰው አምሳያ ነበረ፤ ከወገቡም ወደ ላይ እንደ ፀዳል ምሳሌ፥ እንደሚያንጸባርቅ አይነት ነበረ።